በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኬኒያው ፕሬዚዳንት፥ በሱዳንም ኾነ በቀጣናው “ወታደራዊ አገዛዝን አንፈቅድም” አሉ


የኬኒያው ፕሬዚዳንት፥ በሱዳንም ኾነ በቀጣናው “ወታደራዊ አገዛዝን አንፈቅድም” አሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:10 0:00

“የምሥራቅ አፍሪካ ክልላዊ ማኅበረሰብ አባል ሀገራት መሪዎች፣ አህጉራችን ወደ ወታደራዊ አገዛዝ እንድትንሸራተት አይፈቅዱም፤” ሲሉ፣ የኬኒያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ተናገሩ፡፡

ሩቶ ይህን ያሉት፣ ባለፈው ማክሰኞ፣ ናይሮቢ ውስጥ በተካሔደ የፍልሰት ጉዳይ ጉባኤ ላይ በአደረጉት ንግግር ላይ ነው፡፡ አገራቸው ኬንያ እና የተቀሩት የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ አባል ሀገራት መሪዎች፣ ሱዳን ውስጥ የሚዋጉትን የሁለቱንም ኃይሎች ወታደሮች ተጠያቂ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡

ክልላዊው ማኅበረሰብ(EAC)፣ እስከ አሁን ውጊያው ለዘለቄታው እንዲቆም ማድረግ ባይችልም፣ እንደ አንዳንድ ተንታኞች እምነት፥ ተፋላሚዎቹ የጦር ጀነራሎች ተቀምጠው እንዲነጋገሩ ግፊት በማድረግ ሊያግዝ ይችላል፡፡

ቪክቶሪያ አሙንጋ ከናይሮቢ ያስተላለፈችው ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል፡፡ ቆንጅት ታየ ታቀርበዋለች፡፡

XS
SM
MD
LG