በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኤል ኒኞ በመጪዎቹ ጥቂት ወራት ምሥራቅ አፍሪካን እንደሚመታ ተጠቆመ


በድርቅ በተመታው አካባቢ የሳምቡሩ ሴት በኬንያ ውሃ ለመቅዳት ወንዝ ወርዳ፣ ሳምቡር፣ ኬንያ እአአ ጥቅምት 21/2022
በድርቅ በተመታው አካባቢ የሳምቡሩ ሴት በኬንያ ውሃ ለመቅዳት ወንዝ ወርዳ፣ ሳምቡር፣ ኬንያ እአአ ጥቅምት 21/2022

ኤል ኒኞ የተባለው የአየር ንብረት ዑደታዊ ለውጥ፣ “በመጪው ሦስት ወራት ውስጥ፣ ምሥራቅ አፍሪቃን ይመታል፤” ሲሉ፣ የግብረ ሠናይ ድርጅቶች እና የሶማሊያ መንግሥት ባለሥልጣናት አስጠነቀቁ።

ከመጠን ያለፈ ዝናም፥ በሶማሊያ፣ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል እና በኬንያ፣ እንዲሁም በሌሎች የምሥራቅ አፍሪካ አካባቢዎች፣ የጎርፍ አደጋ ሊያስከትል ይችላል፤”

“ከመጠን ያለፈ ዝናም፥ በሶማሊያ፣ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል እና በኬንያ፣ እንዲሁም በሌሎች የምሥራቅ አፍሪካ አካባቢዎች፣ የጎርፍ አደጋ ሊያስከትል ይችላል፤” ሲሉ፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብ እና እርሻ ፕሮግራም ባለሥልጣናት አስጠንቅቀዋል።

የኤል ኒኞ የአየር ንብረት ዑደታዊ ለውጥ እና ከጥቅምት እስከ ታኅሣሥ ከሚቆየው የአካባቢው የዝናም ወራት ጋራ በመገጣጠሙ፣ በሶማሊያ ብቻ ቁጥሩ 1ነጥብ2 ሚሊዮን የሚደርስ ሕዝብ ሊጎዳ እንደሚችል ግምት አሳድሯል።

ከሁለቱ ታላላቅ ወንዞች ጁባ እና ሸበሌ አቅራቢያ የሚኖሩ የማኅበረሰብ አባላትም፣ የጥንቃቄ ርምጃዎችን እንዲወስዱና በከፍታ ቦታዎች እንዲቆዩ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል። ሰዎች የኤል ኒኞን መምጣት “በቁም ነገር ሊያጤኑትና ተገቢ ርምጃ ለመውሰድም እንቅስቃሴ መጀመር አለባቸው፤” ሲሉ፣ የድርጅቱ የምሥራቅ አፍሪካ ቢሮ ባልደረባ ፓኦሎ ፓሮን አሳስበዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG