በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዝነኛዋ የህንድ ቦሊውድ ተዋናይት ሕይወቷ ያለፈው ውሃ ውስጥ ሰጥማ ነው


የህንድ ቦሊውድ ተዋናይት ስሪዴቪ ካፑር
የህንድ ቦሊውድ ተዋናይት ስሪዴቪ ካፑር

ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ የሞተችው ዝነኛዋ የህንድ ቦሊውድ ተዋናይት ስሪዴቪ ካፑር ሕይወቷ ያለፈው ውሃ ውስጥ ሰጥማ መሆኑን የዱባይ ፖሊሶች አስታወቁ።

ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ የሞተችው ዝነኛዋ የህንድ ቦሊውድ ተዋናይት ስሪዴቪ ካፑር ሕይወቷ ያለፈው ውሃ ውስጥ ሰጥማ መሆኑን የዱባይ ፖሊሶች አስታወቁ።

ቀደም ሲል በወጡ ሪፖርቶች ተዋናይቱ የሞተችው በልብ ድካም ነው ብለው ነበር።

በተካሄደው ምርመራ ህንዳዊቱ ተዋናይት ህይወትዋ ያለፈው በሆቴል ክፍሏ ባኞ ውስጥ ራሱዋን ከሳተች በኋላ ውሃው ውስጥ ሰጥማ ነው ሲል ፖሊስ በትዊተር አስታውቁዋል።

የሃምሳ አራት ዓመትዋ ስሪዴቪ ባለፈው ቅዳሜ ዱባይ የተገኘቸው አክስት የምትሆነውን ሙሽራ ሰርግ ለማክበር እንደነበር ተዘግቧል።

ቻንዲኒ ላምሄ ሚስተር ኢንዲያ እና ናጂና የሚሉትን ጨምሮ በበርካታ የህንድ የፍቅር ፊልሞች የምትታወቀው ተዋናይት ሦስት መቶ በሚበልጡ ፊልሞች ተካፍላለች። አስከሬንዋ ዛሬ ሰኞ ወደሙምባይ ተልኳል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG