በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ከፌዴራል መንግሥት ጋር እስካሁን የተጀመረ ድርድር የለም” - ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል


 “ከፌዴራል መንግሥት ጋር እስካሁን የተጀመረ ድርድር የለም” - ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:28 0:00

ከፌዴራል መንግሥት ጋር እስካሁን የተጀመረ ድርድር እንደሌለ ትግራይ ክልልን በማስተዳደር ላይ የሚገኙት ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል ገለፁ። የትግራይ ክልል ሕዝብ ሳያውቅ እና ሳይወስን የሚያካሂዱት ድርድር እንደሌለም ተናግረዋል።

ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለትግራይ ክልል መገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ፤ “የኤርትራ መንግሥት እስካሁን የትግራይን ክልል አካባቢዎች ተቆጣጥሮ ይዟል” ብለዋል። “ይህንንም ለቆ ሊወጣ ይገባል” ሲሉ አሳስበዋል። ብለዋል።

በሌላ በኩል ትናንት ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ሰላምን ማውረድ እንደሚፈልግ ገልፀው ይህንን በስኬት ለማጠናቀቅ የሚረዳ ስለ ጉዳዩ ጥናት የሚያደርግ ኮሚቴ ተዋቅሮ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል።

በግንቦት አጋማሽ መግለጫ ያወጣው የኤርትራ መንግሥት በበኩሉ ህወሓት በአፍሪካ ቀንድ ቀውስ ለመፍጠር በኤርትራ ላይ ጦርነት አውጇል ሲል መወንጀሉ ይታወሳል።

/ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG