በዚህ በኩል ግዙፎቹ የተቃጠለው ካርዶን አምራቾችና የአባባቢ አየር በካዮች የልቀት መጠናቸውን በ1990ዎቹ ዓመታት ከነበረበት መጠን በ5 ከመቶ መቀነስ እግዳለበት የሚያዘው የኪዮቶ ፕሮቶኮል እየተባለ የሚጠራው ስምምነት ዕጣ ፈንታ ነበር፡፡
ይህ ላለፉት 154 ዓመታት ሥራ ላይ የቆየ ስምምነት ኃይሉ የሚያበቃው በያዝነው የአውሮፓዊያን ዓመት፣ ማለትም በያዝነው ዲሴምበር ወር መጨረሻ ላይ ነው፡፡
የኪዮቶው ስምምነት ምንም እንኳ ተፈልጎ እንደነበረው አስገዳጅ አቅም አይኑረው እንጂ እአአ በ1997 ዓ.ም የጃፓንዋ ኪዮቶ ከተማ ላይ ሲፈረም በኢንዱስትሪ የተራመዱ በአብዛኛው የአውሮፓ ሃገሮች የጋዝ ልቀት መጠናቸውን በተጠየቀው መሠረት እንዲቀንሱ ተጠብቆ የነበረው በስምምነቱ ማብቂያ ጊዜ ባለፉት ከ2008 እስከ 2012 ባሉት አምስት የመጨረሻ ዓመታት ነበር፡፡
የኪዮቶ ፕሮቶኮል ግን የተጠበቀበትን ውጤት አላስገኘም፡፡
ዘገባውን ያዳምጡ፡፡