በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ፦ ያለፉ ጉባዔዎች ግምገማ


ፕሮፌሰር ቡሩክ ኃይሉ /በግራ/፤ አቶ ተድላ አስፋው /በቀኝ/
ፕሮፌሰር ቡሩክ ኃይሉ /በግራ/፤ አቶ ተድላ አስፋው /በቀኝ/

የዩናይትድ ስቴትስ አጠቃላይ ምርጫ ሂደት በይፋ ተጀምሯል። የቅድሚያ ድምፅ አሰጣጥ እየተካሄደ ነው። ለዋናው የምርጫ ዕለት የቀሩት ሰላሣ አራት ቀናት ብቻ ናቸው። ባለፈው ወር መጨረሻ የተካሄዱት የሁለቱ አውራ ፓርቲዎች /የሪፐብሊካኑና የዴሞክራቲክ/ ጉባዔዎች ዕጩዎቻቸውን አሳውቀው ሁለቱ ተገዳዳሪዎች፤ ተቀማጩ ፕሬዚዳንት ዶናል ትረምፕ እና የቀድሞው ምክትል ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በዚህ ምሽት የመጀመሪያ የግንባር ክርክራቸውን ይገጥማሉ።

የሁለቱ እሰጥ አገባ በሦስት ዙሮች የሚካሄዱ ሲሆን የአሁኑ ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስና የዴሞክራቲክ ፓርቲው ዕጩ ካማላ ሃሪስ አንድ ክርክር ይኖራቸዋል።


በየወገናቸው ዕጩዎቻቸውን አፅድቀው ያሳወቁት ሁለቱ ፓርቲዎች ባካሄዷቸው ያለፉ ጉባዔዎቻቸው ላይ ተቺዎችንና ተንታኞችን ጋብዘን አነጋግረናል።

የሰሜን ካሮልይና ዩኒቨርሲቲው የፖለቲካ ሳይንስ መምህርና የፉልብራይት ስኮላር ፕሮፌሰር ቡሩክ ኃይሉ የጉባዔዎቹን አጠቃላይ አካሄድ፣ ቅርፅና ይዘት ገምግመዋል። እንዲሁም “ትረምፕ በእውኑ የሰላም፣ የሥራ፣ የሥርዓትና የህግ ፕሬዚዳንት ናቸው” ብለው እንደሚያምኑ የሚናገሩት የኒው ዮርኩ አቶ ተድላ አስፋውም ለፕሬዚዳንቱ ያላቸውን ድጋፍ በገለፁበት ማብራሪያቸው በተቃራኒው በጆ ባይደን፣ በዴሞክራቲክ ፓርቲውና በዴሞክራቲክ ባለሥልጣናት ላይ ያላቸውን ትችትም አሰምተዋል።

የሁለቱም ግምገማዎችና አስተያየቶች ቀደም ሲል በራዲዮ ሥርጭቶቻችን የተደመጡ ቢሆንም ከዛሬው ክርክር በፊት ማገናዘቢያ ይኖርዎ ዘንድ ከተያያዙት የድምፅ ፋይሎች ሁለቱም በተናጠል የሰጧቸውን ትንታኔዎች እንዲያዳምጡ እንጋብዛለን።

ፕሮፌሰር ቡሩክ ኃይሉ ስለ ዴሞክራቲክና ሪፐብሊካን ፓርቲዎች ጉባዔዎች - ትንታኔ
please wait

No media source currently available

0:00 0:49:47 0:00

አቶ ተድላ አስፋው /የፕ. ዶናልድ ትረምፕ ደጋፊ/ ስለ ዴሞክራቲክና ሪፐብሊካን ፓርቲዎች ጉባዔ 2020
please wait

No media source currently available

0:00 0:55:02 0:00

XS
SM
MD
LG