በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በድሬዳዋ ሁከትና ረብሻ የተጠረጠሩ ፍ/ቤት ቀረቡ


በድሬዳዋ ከሳምንት በፊት ተቀስቅሶ በነበረው ተቃውሞ ሁከትና ረብሻ አስነስተዋል፣ ከተባሉት መካከል 155ቱ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፤

በድሬዳዋ ከሳምንት በፊት ተቀስቅሶ በነበረው ተቃውሞ ሁከትና ረብሻ አስነስተዋል፣ ንብረት አጥፍተዋል ብሎ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ካዋላቸው ተጠርጣሪዎች መካከል 155ቱ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፤ ተጠርጣሪዎቹ በማቆያ ፖሊስ ጣቢያነትም ሆነ በማረሚያ ቤትነት በማይታወቅ ካምፕ መታሰራቸው ተቃውሞ አስነስቷል፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም ዕድሜያቸው 13ና 14 የሆኑ ሦስት ታዳጊዎች እንዲሁም አንድ በፅኑ ህመም ላይ የሚገኝ ተጠርጣሪ በዋስ እንዲለቀቁ የወሰነ ሲሆን ቀሪዎቹ ለየካቲት 4 እና 5 እንዲቀርቡ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

በከተማዋ የሚገኙ 12 አድባራት ሰበካ ጉባዔዎችም በቁጥጥር ሥር ያሉ ተጠርጣሪዎች ጉዳይ በይቅርታ እንዲዘጋ መጠየቅ ጀምረዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በድሬዳዋ ሁከትና ረብሻ የተጠረጠሩ ፍ/ቤት ቀረቡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:16 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG