ላለፉት አምስት ቀናት በድሬደዋ የዕለት-ተዕለት እንቅስቃሴዎችን አስቁሞ የሰነበተው ተቃውሞ ዛሬ ከተማይቱ ተረጋግታ መዋሏ ተዘገበ፡፡
የአስተዳደሩ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የከተማዋን ፀጥታ የማስከበሩን ስራ ከትላንትና አመሻሽ ጀምሮ የምስራቅ እዝ ጠቅላ መምሪያ በበላይነት እንዲመራው መወሰኑን ገልጿል፡፡
የአስተዳደሩ ፖሊስ ኮሚሽን በተለይ ለአሚሪካ ድምጽ በሰጠው መግለጫ እንዳመለከተው በተቃውሞ እንቅስቃሴው የተወሰነ ንብረት ከመውደሙና ሶስት ሰዎች ከመቁሰላቸው በስተቀር ሰላማዊ ነበር ብሏል፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ