በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስለአማራ ተፈናቃዮች - ሠልፍ በዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት


ስለአማራ ተፈናቃዮች የኢትዮጵያዊያንና ኢትዮጵያዊያን-አሜሪካዊያን ሠልፍ በዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት
ስለአማራ ተፈናቃዮች የኢትዮጵያዊያንና ኢትዮጵያዊያን-አሜሪካዊያን ሠልፍ በዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት

ዋሺንግተን ዲ.ሲ. አካባቢ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊያንና ኢትዮጵያዊያን-አሜሪካዊያ ዛሬ ሰኞ በዋይት ሀውስ ቤተመንግሥት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው የኢትዮጵያ መንግሥት በተለይ በአማራው ተወላጆች ላይ «ያካሂዳል» ያሉትን ማፈናቀልና ማዋከብ ተቃውመዋል።
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:49 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት
ዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት

ዋሺንግተን ዲ.ሲ. አካባቢ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊያንና ኢትዮጵያዊያን-አሜሪካዊያ ዛሬ ሰኞ በዋይት ሀውስ ቤተመንግሥት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው የኢትዮጵያ መንግሥት በተለይ በአማራው ተወላጆች ላይ «ያካሂዳል» ያሉትን ማፈናቀልና ማዋከብ ተቃውመዋል።

«ሕወሓት ኢትዮጵያ ውስጥ የዘር ማፅዳት ዘመቻ እያካሄደ ነው» የሚሉት ሰላማዊ ሠልፈኞቹ «የፕሬዚደንት ኦባማ አስተዳደር ይህን መንግሥት መርዳቱን ያቁም» ሲሉም ይጠይቃሉ።

“- ክቡር ፕሬዚደንት፣ ዛሬ እዚህ የተሰለፍንው፣ ስለ ወገኖቻችንን ለመናገር ነውና ያድምጡን!
“- ክቡር ፕሬዚደንት፣ ኢትዮጵያ የሚገኙ ወገኖቻችን ይገደላሉ፣ ይሳደዳሉ፣ ይፈናቀላሉ!
“- አሜሪካ፤ ሕወሓትን በገንዘና በቁሳቁስ በመርዳትሽ ተጠያቂ ነሽ!
“- አሜሪካ፤ ሕወሓት ኢትዮጵያ ውስጥ የዘር ማፅዳት ዘመቻ ይዟል!
“- ክቡር ፕሬዚደንት፣ ሕወሓት የአማራውን ሕዝብ ያለ ወንጀሉ እየገደለ፣ እያንገላታና እያፈናቀለ ነው!”
ሌሎችም በርካታ መፈክሮች በእንግሊዝኛ ተሰምተዋል። ቢያንስ 450 የሚሆኑ ሠልኞች ነበሩ።

ከዲ.ሲ.ና አካባቢዋ በተጨማሪ ከፊላዴልፊያ፣ ከካሮላይና ባጠቃላይ ከዋሽንግተን ከአራት መቶ ኪሎ ሜትሮች በላይ ርቀት ካላቸው ቦታዎች ጭምር የተሰባሰቡት ሰላማዊ ሠልፈኞች የዛሬ ዋነኛ ዓላማቸው “የአማራ ተወላጆች ለዓመታት ከኖሩባቸው አካባቢዎች በመንግሥት ተፈናቅለዋል፤ ተሳደዋል” በማለት ተቃውሟቸውን ለዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ለማሳወቅ ነው።

የሰልፉ አስተባባሪና ቃል-አቀባይ ልጅ ሠይፈ-ሚካኤል ዘውዴ እንደገለፁት ይህ ዓይነቱ ሰልፍ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በተለያዩ ስቴቶች የሚቀጥል ከመሆኑም በላይ በአውሮፓና በአውስትራሊያም እንዲካሄድ ሁኔታውን እያመቻቹ ናቸው።

በዛሬው ሠልፍ ላይ “ከሃያ የሚበልጡ የሕዝባዊ ድርጅቶችና የፖለቲካ ፓርቲዎች ወኪሎች ተካፋይ ናቸው” ያሉ አንዱ አዘጋጅ “ለምሳሌ ጥቂቶቹን …” ብለው ሲገልፁ “የሸንጎው፣ የኢሕአፓ ወጣት ክንፍ፣ የሽግግር ምክር ቤት፣ የኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ሕብረት፣ ያዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ፣ ዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የሚገኙ የኢትዮጵያውያን ራዲዮ ጣቢያዎች ተወካዮች፣ ወዘተ” ብለዋል።

የተለያዩ የሃይማኖት ድርጅቶች ተወካዮችም መገኘታቸው ተገልጿል፡፡

የሰልፉ አዘጋጆች፣ ይህንኑ ጉዳያቸውን የተመለከተውንና ለፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ በአድራሻቸው የጻፉትን ደብዳቤም እንዳስገቡ አመልክተዋል። “የተከበሩ ውድ ፕሬዚደንት፤ እኛ በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የምንኖር ኢትዮጵያዊያን-አሜሪካዊያን ከሁሉ አስቀድሞ፣ በመጀመሪያዎቹ አራት የፕሬዚደንትነት ዘመንዎ ያደረጉትን አስተዋፅዖና ይልቁንም አገሪቱን ከከፍተኛ ግሽበት ለማዳን ያሳዩትን ብቃት ያለው አመራር ማድነቅና ድጋፋችንንም መግለፅ እንወዳለን» ብሎ የጀመረው ደብዳቤ፣ «ብዙ ጊዜ ዝናብ ሆነ ፀሐይ፣ ክረምት ሆነ በጋ፣ ብርድ ሆነ ሙቀት ከቤተ-መንግሥትዎ ደጃፍ እየቆምን፣ የወገኖቻችንን ብሦት፣ መከራና ሰቆቃ እናሰማለን። ዛሬም እነሆ መጥተናልና ያድምጡን» ብሏል።

በመቀጠልም በአንድ ወቅት በራስዎ አንደበት «በሙስና ሥልጣን ላይ ለተፈናጠጣችሁና የተቃዋሚዎችን አንደበት ለምትዘጉ መሪዎች ሁሉ! ከታሪክ ሂደት ተቃራኒ ላይ የቆማችሁ መሆናችሁን ልታውቁ ይገባል» ማለትዎን በአክብሮት እናስታውሳለን» በማለት በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ያነጣጠረውን ተቃውሟቸውን በስፋት ዘርዝሯል።

ከሰልፈኞቹ መካከልም አንዳንዶቹ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

የኢትዮጵያዊያኑንና የኢትዮ-አሜሪካዊያኑን ሰልፍ የተከታተለው አዲሱ አበበ ነው፤ የተያያዘውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG