በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም የንግድ፣ የመንግሥታት ተወካዮችና የማኅበረሰብ ተቋማት በጂኒቫ እየተወያዩ ነው

ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

በዚህ ሳምንት ከሠባት መቶ በላይ የሚሆኑ የዓለም የንግድ፣ የመንግሥታት ተወካዮችና የማኅበረሰብ ተቋማት በጂኒቫ ተሰባስበው፤ በማደግ ላይ ያሉ ሀገሮች በድረ ገፅ ንግድ ዙሪያ ያሉ ዕድሎችና ፈተናዎችን በመገምገም ላይ ናቸው።

በዚህ ሳምንት ከሠባት መቶ በላይ የሚሆኑ የዓለም የንግድ፣ የመንግሥታት ተወካዮችና የማኅበረሰብ ተቋማት በጂኒቫ ተሰባስበው፤ በማደግ ላይ ያሉ ሀገሮች በድረ ገፅ ንግድ ዙሪያ ያሉ ዕድሎችና ፈተናዎችን በመገምገም ላይ ናቸው።

ከ65 ሀገሮች የተሰበሰቡት ተሳታፊዎች በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የንግድና ልማት ተቋም /UNCTAD/ ጋባዥነት ነው።

ጊዜው የድረ ገፅ ንግድ ነው። በዓለም ዙሪያ ሸማቾች ወደ ገበያ፣ ጉልት፣ ሞል፣ አትክልት ተራና መርካቶ በእግር፣ በፈረስና በመኪና መጓዝ ሳይኖርባቸው፤ በኮምፒውተር መስኮት የፈልጉትን ሁሉ የሚገዙበት ኢ-ኮመርስ የገበያ ድርሻው ተስፋፍቷል።

በተለይ ከሁለት ዓመት በፊት አጠቃላይ የዓለም ገበያ ላይ 25 ትሪሊየን ዶላርስ ድርሻ ይዟል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም ይሄ እያደገ ያለ የገበያ መድረክ በማደግ ላይ ለሚገኙ ሀገሮች የሚኖረውን ጥቅም ለመመርመር ለአንድ ሣምንት የሚዘልቅ ጉባዔ አዘጋጅቷል። ሊሳ ሽላይን ከስፍራው ያደረሰችንን ሔኖክ ሰማእግዜር ያቀርበዋል።

የዓለም የንግድ፣ የመንግሥታት ተወካዮችና የማኅበረሰብ ተቋማት በጂኒቫ እየተወያዩ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:40 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG