በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የረሃብ አዙሪት እንዴት ይሠበር?


አቶ ደሣለኝ ራሕመቶ ከቪኦኤ አድማጮች ጋር ይነጋገራሉ፡፡

ለአድማጮች ጥያቄ መልስ የሚሰጡት አቶ ደሣለኝ ራህመቶ ናቸው። አቶ ደሣለኝ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለረጅም ዓመታት በመምህርነትና የዩኒቨርሲቲውን የማህበራዊ ጥናት ተቋም በመምራት ያገለገሉ ምሁር ናቸው።

አቶ ደሣለኝ እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ1997 ዓም ከዩኒቨርሲቲው በጡረታ እንዲሰናበቱ ከተደረገ ወዲህ፣ ከሙያ ባልደረቦቻቸው ጋር በመተባበር ”የማህበራዊ ጥናት መድረክ” የተባለ ነፃና ገለልተኛ ተቋም መሥርተው በገጠር ልማት፣ በመሬት ይዞታ፣ በምግብ ዋስትና፣ በዓየር ጠባይና ልማት፣ በአስተዳደርና ሲቪል ማህበረሰብ ጥናትና ምርምር ቀጥለዋል።

በርካታ ፅሁፎችና መፅሐፍትን አበርክተዋል፤

የ"ለጥያቄዎ መልስ" ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ ትዝታ በላቸው "የረሃብ አዙሪት እንዴት ይሠበር?" በሚል ርዕስ ላይ ለመነጋገር ጋብዛቸው አቶ ደሣለኝ ለአድማጮች ጥያቄዎች መልስ ሰጥተዋል፡፡

ዝርዝሩን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG