No media source currently available
የግብፁ ጦር ዋና አዛዥ ብርጌዲየር ጅነራል ሞሃመድ ሳሚርሰኢድ በዛሬው ዕለት በፌስ ቡክ ላይ ባሰፈሩት ቃል፣ ከመንገደኞቹ የግል ንብረቶች መካከል አንዳንድ ነገሮች እንደተገኙና የአርፕላኑ ስብርባሪዎችም ባሕሩ ላይ ተንሳፈው መታየታቸውን አመልክተዋል። አሮፕላኑ ከራዳር እይታ ከተሰወረበት አካባቢ ጥቂት ፈቀቅ ብሎ በሚገኝ ስፍራ ደግሞ፤ አንዳንድ የሰውነት ክፍሎች፣ ወንበሮችና ሻንጣዎች መገኘታቸውን የአቴንስ-ግሪክ ባለሥልጣናት ይናገራሉ።