በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአቢዬይ ሰላም አስከባሪ ተግባሩን ‘እየተወጣ አይደለም’ ሲሉ የደቡብ ሱዳን ባለሥልጣን ወቀሱ


ኩዎል ዴንግ ኩዎል - የንጎክ-ዲንካ ጎሣ የበላይ መሪ
ኩዎል ዴንግ ኩዎል - የንጎክ-ዲንካ ጎሣ የበላይ መሪ



please wait

No media source currently available

0:00 0:11:08 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

አቢዬይ
አቢዬይ
የንጎክ-ዲንካ ጎሣ የበላይ መሪ የሆነት ኩዎል ዴንግ ኩዎል የተገደሉት ከትናንት በስተያ ቅዳሜ ከሱዳን ባለሥልጣናት ጋር ተወያይተው እየተመለሱ ሳሉ ነበር፡፡

በአካባቢው በከብት አርቢነትና በተንቀሣቃሽነት የሚኖሩት የምስሪያ ጎሣ አባላት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባንዲራ ታጅቦ ይጓዝ በነበረ የሚስተር ኩዎል ዴንግ የልዑካን ቡድን ላይ ከፍተውታል በተባለው ድንገተኛ የደፈጣ ጥቃት ከራሣቸው ከጎሣው መሪ ሌላ የተባበሩት መንግሥታት የላም አስከባሪ ኃይል አባል የሆነ አንድ የኢትዮጵያ ወታደር ተገድሎ ሌሎች ሁለት ኢትዮጵያዊያን ወታደሮች መቁሰላቸው ታውቋል፡፡ የጎሣው መሪ ኩዎል ዴንግ ተሣፍረውበት የነበረው መኪና አሽከርካሪም መገደሉ ተነግሯል፡፡

አድራጎቱን ኢትዮጵያ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ የአፍሪካ ሕብረትና ዩናይትድ ስቴትስ አውግዘውታል፡፡

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም አድራጎቱን እንደሚያወገዙ ያስታወቁት በትዊተር ገፃቸው ላይ ባወጡት መልዕክት ነው
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም አድራጎቱን እንደሚያወገዙ ያስታወቁት በትዊተር ገፃቸው ላይ ባወጡት መልዕክት ነው
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም አድራጎቱን እንደሚያወገዙ ያስታወቁት በትዊተር ገፃቸው ላይ ባወጡት መልዕክት ነው፡፡
ኮሎኔል ፊሊፕ አጉየር
ኮሎኔል ፊሊፕ አጉየር

የደቡብ ሱዳኑ የሱዳን ሕዝብ አርነት ጦር - ኤስፒኤልኤ ቃል አቀባይ ኮሎኔል ፊሊፕ አጉየር በሰጡት ቃል የቅዳሜው አጋጣሚ ያሚያሣየው “የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአቢዬይ የሽግግር የፀጥታ ኃይል - ዩኒስፋ ሥራውን በአግባቡ እየተወጣ አለመሆኑን ነው” ሲሉ ወቅሰዋል፡፡

የአፍሪካ ሕብረት ባወጣው ይፋ መግለጫ ግድያውን በፅኑ እንደሚወግዝ አስታውቋል፡፡

ዶ/ር ንኮሣዛና ድላሚኒ ዙማ - የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር
ዶ/ር ንኮሣዛና ድላሚኒ ዙማ - የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር
የሕብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ዶ/ር ንኮሣዛና ድላሚኒ ዙማ ዜናው እንዳስደነገጣቸው ተናግረው የሱዳን መንግሥት ተጠያቂዎችን በአስቸኳይ ለፍትሕ እንዲያቀርብ ጠይቀዋል፡፡

ባን ኪ-ሙን - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ
ባን ኪ-ሙን - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ባን ኪ ሙንም እንዲሁ የቺፍ ዴንግ ኩዎል ዴንግን እና የሰላም ጥበቃ ኃይላቸውን አባል መገደል አውግዘው ለንጎክ-ዲንካ ጎሣ፣ ለኢትዮጵያ መንግሥትና ለተገደሉት ቤተሰቦች ኀዘናቸውን ገልፀዋል፡፡

የሁለቱ ሱዳኖች መንግሥታትና የንጎክ ዲንካ ማኅበረብ አባላት መረጋጋት እንዲኖራቸው ሚስተር ባን ጠይቀዋል፡፡

ሱዛን ፔጅ - በደቡብ ሱዳን የአሜሪካ አምባሣደር
ሱዛን ፔጅ - በደቡብ ሱዳን የአሜሪካ አምባሣደር
አድራጎቱን ዩናይትድ ስቴትስም እንደምታወግዘው በደቡብ ሱዳን የአሜሪካ አምባሣደር ሱዛን ፔጅ አመልክተዋል፡፡

ለተጨማሪና ዝርዝር መረጃ፤ እንዲሁም የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ዲና ሙፍቲ የሰጡትን መግለጫ የያዘውን ቃለምልልስ ከተያያዘው ዘገባ ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG