ዋሺንግተን ዲሲ —
የዲሞክራሲ በተግባር እንግዳ የሕዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ መስራች አባል አንጋፋው አስገደ ገብረሥላሴ በውጊያ፣ በአዋጊነት፣ በስንቅና ትጥቅ አከፋፋይነትና በውጊያ አሰልጣኝነት ለ17 ዓመታት አገልግለዋል።
“መሣሪያ አንስተን ወደ በረሃ ለትግል የገባነው የሃገሪቱን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ በተለይም የባህር በሮቿን ባለቤትነት ለማስከበር፣ ደርግን አስወግደን፣ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመመሥረት እንጂ የህወሃት መሪዎች ሥልጣን ከያዙ በኋላ እንዳደረጉት ኤርትራን ለማስገንጠል አልነበረም” ሲሉ በቁጭት ይናገራሉ።
አቶ አስገደ ከሠላሳ ሺህ በላይ ታጋዮች ጋር ከድርጅቱ እንዲሰናበቱ ከተደረገ በኋላ አሁን ምን ይሠራሉ?
ለህክምና ዋሺንግተን ዲሲ የሚገኙትን አቶ አስገደ ገብረሥላሴን ሰሎሞን ክፍሌ አነጋግሯቸዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ