No media source currently available
ከደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ በፀጥታ ስጋት ምክንያት ወደ ቤተሰቦቻቸው ተመልሰው ከነበሩ ስምንት መቶ ተማሪዎች አብዛኞቹ ወደ ትምህርት ገበታቸው መመለሳቸውን የዩኒቨርሲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ለታ ተስፋዬ አስታውቀዋል። ግቢውን ለቅቀው ወጥተው የነበሩት ተማሪዎች ከአማራ ክልል ብቻ የሄዱ እንደነበሩ ተደርጎ የነበረውም እውነት እንዳልሆነና ተማሪዎቹ ከሁሉም ከአገሪቱ አካባቢዎች የሄዱ መሆናቸውንም ፕሬዚዳንቱ ገልፀዋል።