በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢንዶኔዥያን ለ3 ቀናት በመታት ጎርፍና የመሬት መንሸራተት የ89 ሰዎች ህይወት አለፈ


የኢንዶኔዥያዋን ምስራቃዊ ፓፑዋ ክፍለ ሀገር በተከታታይ ለሦስት ቀናት በመታት ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት ሰማኒያ ዘጠኝ ሰዎች መሞታቸውን የአጣዳፊ ዕርዳታ ባለሥልጣናት ገለጹ።

ሴንታኒ በተባለችው ከተማ ቅዳሜ ዕለት በጣለው ከባድ ዝናብ ከፍታ ካላቸው አካባቢዎች ጭቃ፣ ዛፍና አለት እየጠራረገ ወደ ወንዝ የወረደው ጎርፍ በከተማዋ ታሪክ ከምንጊዜውም የከፋ መሆኑ ተነግሯል።

ወንዞች ሞልተው በርካታ መኖሪያ ቤቶችንና መንገዶችን ወስደዋል። ቢያንስ ሰባ አራት ሰዎች የደረሱበት ጠፍቷል። ብዙዎች ቆስለዋል፣ በአደጋው ሰባት ሺህ የሚሆን ሰው ያለመጠጊያ ቀርቶ በጊዚያዊ ካምፖች ተጠልሏል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG