No media source currently available
የዩናይትድ ስቴትስ የመጀመሪያው ጥቁር የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር እና የመጀመሪያው ጥቁር ኤታማዦር ሹም ኮሊን ፖል ዛሬ አርፈዋል፡፡ ጄነራል ፖል ያረፉት በኮቪድ 19 ምክንያት በህክምና ላይ ከቆዩ በኋላ ነው፡፡ ኮሊን ፖልን በስራ አጋጣሚ የሚያውቋቸው የኢትዮጵያ የቀድሞ ከፍተኛ ዲፕሎማት እና በኖርዝ ካሮላይና ግዛት መምህር የሆኑት ዶ/ር ብሩክ በሻህ ኮሊን ፖል እንደ ፖለቲከኛ እና የጦር መሪ ስለነበራቸው ማንነት ከአሜሪካ ድምጽ ጋር አጭር ቆይታ አድርገዋል፡፡