በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኒው ዮርክ ከተማ መኖሪያ ሕንፃ ላይ በደረሰ ቃጠሎ የአሥራ ሁለት ሰዎች ሕይወታቸው አለፈ


ዩናይትድ ስቴትስ ኒው ዮርክ ከተማ ብሮንክስ ቀበሌ የሚገኝ የመኖሪያ ሕንፃ ላይ ትናንት ሃሙስ በደረሰው ቃጠሎ አሥራ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን የከተማዋ የእሳት አደጋ ኮሚሽነር ገለጡ፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ኒው ዮርክ ከተማ ብሮንክስ ቀበሌ የሚገኝ የመኖሪያ ህንፃ ላይ ትናንት ሃሙስ በደረሰው ቃጠሎ አሥራ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን የከተማዋ የእሳት አደጋ ኮሚሽነር ገለጡ፡፡

ቃጠሎውን ያስነሳው እንድ የሦስት ዓመት ተኩል ህፃን ልጅ በምግብ ማብሰያው ምድጃው ሲጫወት መሆኑን ገልፀዋል።

ቃጠሎው ሲነሳ እናት ልጆችዋን ይዛ በሩን ክፍት በመተው ስትሸሽ እሳቱ ፈጥኖ መዛመቱ ተገልጿል።

ባለ አምስት ፎቁ ህንፃ ካሁን ቀደምም የተበላሹ የካርቦን ሞኖ ኦክሳይድ ጋዝ ብክለትን እና የእሳት አደጋ ቅድሚያ ማስጠንቀቂያዎችን ጨምሮ የህንፃ ደኅንነት ጥሰት ሪፖርቶች የነበሩበት መሆኑን ባልሥልጣናቱ ገልፀዋል፡፡

የእሳት አደጋ ሰራተኞች በሦስት ደቂቃ ውስጥ እንደደረሱ ነው የተገለጠው። የእሳት አደጋው ኮሚሽነር እንደተናገሩት የሞቱት ሰዎች ብዛት በሃያ አምስት ዓመታት ውስጥ ኒው ዮርክ ውስጥ በእሳት አደጋ ከሞቱት ሁሉ ከፍተኛው ነው።

የተቃጠለው ሕንፃ የሚገኘው ከታዋቂው የብሮንክስ የዱር እንስሳት መጎብኛ አካባቢ ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG