አዲስ አበባ —
መኢአድ እና አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ “የመተዳደሪያ ደንቦቻቸውን የጣሱ የአመራር ምርጫዎች አካሂደዋል” ያለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ “የውስጥ ችግሮቻችሁን ፍቱ” በሚል ለሁለቱ ፓርቲዎች የሰጠው የሁለት ሣምንታት ቀነ ገደብ ማክሰኞ፤ ጥር 19/2007 ዓ.ም ተጠናቅቋል፡፡
ሁለቱ ፓርቲዎች በተደጋጋሚ በሰጧቸው መግለጫዎች ምርጫ ቦርድ በውስጥ ጉዳያችን ጣልቃ እየገባ ነው ሲሉ ስሞታ አሰምተዋል፡፡
የቀነ ገደቡን መጠናቀቅ አስመልክቶ እስክንድር ፍሬው የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደምሰው በንቲን በስልክ አነጋግሯል፡፡
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡