ዋሺንግተን ዲሲ —
ባለፈው ቅዳሜ በሰሜን ምሥርቅ ናይጀርያ በታጠቁ ሽፍቶችና በመንደር ነዋሪዎች መካከል በተካሄደ ግጭት 45 ሰዎች ተገድለዋል።
ሽፍቶቹ ካዱና በተባለው ሰሜናዊ ክፍለ፡ሀገር በሚገኘው ግዋስካ ድንበር ላይ ጥቃት ከፈቱ። የአካባቢ ጥበቃ ኃይል አባል የሆነ ሰው በተናገረው መሰረት ሽፍቶቹ የጥበቃ ኃይሉን በማጥቃት በልጆች ላይ ተኩስ ከፍቷል። መኖርያ ቤቶችንም በእሳት አጋይተዋል።
ማንነቱ ያልተገለፀው የጥበቃ ኃይል አባል አጥቂዎቹ በአቅራቢያው ከሚገኘው ዛምፋራ ክፍለ፡ሀገር የመጡ ናቸው ብሏል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ