No media source currently available
“የኦሮሞ ሴቶች ሰልፍ በዲሲ” በሚል የተጠራው የቃውሞ ሰልፍ በዛሬው ዕለት በዋሽንግተን ዲሲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ፊት ለፊት ተካሂዷል፡፡ የሰልፉ ዓላማ ድምጽ ለሌላቸው የኦሮሞ ሴቶች ድምጽ ለመሆን ነው” ያሉት ሰለፈኞቹ እስረኞች ይፈቱ፣ የኦሮሞ ሴቶችን መድፈር ይቁም የኢትዮጵያ መንግሥት የኦሮምን ህዝብ መግደል ያቁም! ፍትህ ለሀጫሉ! የመሳሰሉ መፈክሮችን አንግበዋል፡፡