በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዳዊት ከበደና ሲፒጄ

ፎቶ ፋይል - ዳዊት ከበደ እአአ በ2010ዓ.ም ዓለምአቀፉን የፕሬስ ነፃነት ሽልማት ሲቀበል
ፎቶ ፋይል - ዳዊት ከበደ እአአ በ2010ዓ.ም ዓለምአቀፉን የፕሬስ ነፃነት ሽልማት ሲቀበል
ፎቶ ፋይል - ዳዊት ከበደ እአአ በ2010ዓ.ም ዓለምአቀፉን የፕሬስ ነፃነት ሽልማት ሲቀበል
ፎቶ ፋይል - ዳዊት ከበደ እአአ በ2010ዓ.ም ዓለምአቀፉን የፕሬስ ነፃነት ሽልማት ሲቀበል

please wait

No media source currently available

0:00 0:08:03 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የ2010 ዓ.ም - በአውሮፓዊያኑ የዘመን አቆጣጠር - የዓለምአቀፍ የፕሬስ ነጻነት ሽልማት ተሸላሚ ኢትዮጵያዊው ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ በምኅፃር ሲፒጄ ተብሎ የሚታወቀውን የጋዜጠኞች ደኅንነት ተሟጋቹን ቡድንና ሌሎች የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶችን “የምዕራባውያን አጀንዳ አስፈፃሚ መሣሪያዎች ናቸው” ብሏቸዋል።

ዳዊት ከ1997ቱ የኢትዮጵያ ምርጫ ጋር ተያይዞ ባቀረባቸው ዘገባዎቹ ታሥሮ ከተፈታ በኋላ በስደት ለሁለት ዓመታት አሜሪካ ቆይቶ ወደ ሀገሩ ተመልሷል።

ዳዊት ኢትዮጵያ ውስጥ በጋዜጠኝነት መሥራት እንደማይቻል ገልፆ ስደት ላይ ከቆየ በኋላ የተመለሰበትን ምክንያት ሲገልፅ ”ባብዛኛው ያለውን መንግሥት ከሚቃወመው ዳያስፖራ የደረሰብኝ ተፅዕኖ፥ ሀገር ውስጥ ካለው ሺህ ጊዜ በመብለጡ ነው” ብሏል።

ዳዊት በቅርቡ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስ መነሻ አድርገን አነጋግረነዋ፤ የምዕራቡን ዓለም አጃንዳ ያራምዳሉ ሲል የወነጀላቸውን የሲቪክ ድርጅቶች ምላሽም ይዘናል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የሰሎሞን ክፍሌን ዘገባ ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG