በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መንግሥት በትግራይ ክልል ያልተገደበ ተደራሽነት እንዲኖር እንደሚሠራ አስታወቀ


መንግሥት በትግራይ ክልል ያልተገደበ ተደራሽነት እንዲኖር እንደሚሠራ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:59 0:00

መንግሥት በትግራይ ክልል ያልተገደበ ተደራሽነት እንዲኖር እንደሚሠራ አስታወቀ

የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል ያልተገደበ ተደራሽነት እንዲኖር እንደሚሠራ ኢትዮጵያ ለዩናይትድ ስቴትስ ማረጋገጧን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ይሁንና የእርዳታ አቅርቦቱ በአግባቡ እንዲደርስ የህወሓት ታጣቂዎች ከያዟቸው የአፋር ክልል አካባቢዎች ለቀው መውጣት እንዳለባቸው፣ በኢትዮጵያ ጉብኝት ላደረጉት የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ዴቪድ ሳተርፊልድ እንደተገለጸላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል፡፡

የትግራይ ክልል ትናንት ባወጣው መግለጫ፤ የትግራይ ሰራዊት ተቆጣጥሮት ከነበረ ኢሪፕቲ የተባለ አከባቢ ሚያዝያ 4/ 2014 ዓ.ም ለቆ መውጣቱን አስታውቋል።

በመግለጫው ላይ ተያይዞ የተነሳውም፤ "ውሳኔው የትግራይ ክልል መንግሥት ጊዚያዊ ግጭት የማቆም እንዲከበርና ያለእንከን ሰብአዊ ድጋፍ እንዲገባ ተጨማሪ የራሱን እርምጃ እየወሰደ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ነው ብሏል"

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቃል አቀባይ፤ የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ፣ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለሰላም ጉዳይ ወደ ኢትዮጵያ በመመላለስ ላይ እንደሚገኙም ገልጸዋል፡፡

የትግራይ ክልል መንግሥት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ከትናንት በስቲያ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጠው መረጃ ለሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት ሲባል በሁለቱ በኩል ግጭት ለማቆም ውሳኔ ከተወሰነ ሃያ ቀናት ቢሆነውም እስከ አሁን ወደ ትግራይ ክልል ሃያ ስድስት ተሽከርካሪዎች ብቻ መግባታቸውን ገልጾ ነበር።

XS
SM
MD
LG