የዩናይትድ ስቴትስ የህዋ ምርምር ማዕከል በአሁኑ ወቅት እያደረጋቸው ካሉ ምርምሮችና ሙከራዎች መካከል አንዱ፣ አንድ ቀን ከህዋ ላይ ተምዘግዝገው መጥተው ምድርን ሊጎዱ ይችላሉ ተብለው የሚገመቱ አለቶችን ወይም ቋጥኞችን መከላከል የሚቻልበትን ሁኔታ የሚመለከት ነው፡፡ በዚህም መሠረት በቅርቡ አንድ የሙከራ ሳታላይት ከምድር አሥራ አንድ ሚሊዮን ኪሎ ሜትር ርቀት ተጉዞ ከአንድ የህዋ አለት ጋር በታለመ መንገድ ለመጋጨት መቻሉን ናሳ ይፋ አድርጓል፡፡
በዚህ ተልዕኮ ውስጥ ከተሳተፉት መሃንዲሶች እና ሳይንቲሰቶች መካከል ትዉልደ ኢትዮጵውያንም ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል አንዱ የኤሮስፔስ ሳይንቲስት ዶ/ር መላክ መኮነን ዘበናይ የሆኑትን እንግዳ አድርገናል፡፡