በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዳግ የኢትዮጵያን እርምጃዎች እንደሚያደንቅ ሊቀመንበሩ አስታወቁ


ጊርት ገት - የለጋሾች የልማት አጋርነት ቡድን የኢትዮጵያው ጥምረት ተባባሪ ሊቀመንበር
ጊርት ገት - የለጋሾች የልማት አጋርነት ቡድን የኢትዮጵያው ጥምረት ተባባሪ ሊቀመንበር

የኢትዮጵያ መንግሥት ሕዝቡን ከድህነት ለማውጣት እያደረገ ያለውን ጥረት እንደሚያደንቁ በምኅፃር ዳግ ተብሎ የሚታወቀው የለጋሾች የልማት አጋርነት ቡድን የኢትዮጵያው ጥምረት ተባባሪ ሊቀመንበር ጊርት ገት አስታውቀዋል፡፡




please wait

No media source currently available

0:00 0:06:56 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ



የኢትዮጵያ መንግሥት ሕዝቡን ከድህነት ለማውጣት እያደረገ ያለውን ጥረት እንደሚያደንቁ በምኅፃር ዳግ ተብሎ የሚታወቀው የለጋሾች የልማት አጋርነት ቡድን የኢትዮጵያው ጥምረት ተባባሪ ሊቀመንበር ጊርት ገት አስታውቀዋል፡፡
ሊቀመንበሩ የግሉ ዘርፍ ኢትዮጵያ ውስጥ የተሰጠውን ቦታ እንዲገመግሙ ተጠይቀውም ሕብረተሰቡን በመሰለው መንገድ ማደራጀት እና የልዕለ-ምጣኔ ኃብቱን ፖሊሲም በመሰለው መንገድ የማውጣት የኢትዮጵያ መንግሥት የራሱ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡
የግሉ ዘርፍ በቂ ትኩረት ባላገኘበት ሁኔታ ግን ኢትዮጵያ ያሏትን ዕምቅ አቅሞች ሁሉ ልታወጣውና ልትጠቀምበት እንደማትችል ሚስተር ገት ለቪኦኤ በሰጡት ቃለምልልስ ላይ አሳስበዋል፡፡
የተጋነነ ነው ተብሎ ሲተች የነበረውን የኢትዮጵያ የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድን አካሄድ እንዲገመግሙ የተጠየቁት ሚስተር ገት ኢትዮጵያ በጣም ድኃ ሃገር በመሆኗና ፈተናዎቿም የበዙ በመሆናቸው ምክንያት መንግሥቷ ግዙፍ ዕቅድ መያዙን ሁልጊዜ እንደሚያደንቁ ገልፀው ሕዝቡን ከድኅነት ለማውጣት የሚያደርገውን ጥረት እንደሚደግፉ አመልክተዋል፡፡
ለጋሾቹ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በመወያየትና በመግባባት እየሠሩ መሆናቸውን ሚስተር ገት ገልፀው ይህ ማለት ግን ልዩነቶች የሉም ማለት እንዳልሆነ ጠቁመዋል፡፡
ሚስተር ገት ለግሉ ዘርፍ ስለተሰጠው የመንቀሣቀሻ ሜዳ፣ በዕድገት ጠቋሚዎች ላይ ስላለው የኢትዮጵያና ዓለምአቀፍ የስሌት ደረጃዎች ልዩነት፣ የወለድ ተመንን በሚመለከትና ሌሎችም አነጋጋሪ ነጥቦች በቃለምልልሱ ወቅት ተነስተዋል፡፡

ዝርዝሩን ከዘገባው ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG