በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ውሎ


ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ በአዲስ አበባ
ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ በአዲስ አበባ

ዓለምአቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በኢትዮጵያ በሳምንቱ መጨረሻ በተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች በአማራና በኦሮሚያ ክልል፤ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ በቀጥታ በተተኮሰ ጥይት ወደ 100 የሚጠጉ ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን እየገለጹ ነው።

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ እስከዛሬ ቀን ድረስ ደርሶናል ባሉት ሪፖርት የ86 ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ሰላማዊ ሰልፍ በተካሄደባቸው አካባቢዎች፤ ሰዎች እየታሰሩ እና ድብደባ እየተፈፀመባቸው መሆኑን ነዋሪዎቹ ይናገራሉ። የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ “ሀገሩ አሁን ተረጋግቷል እንዲህ ያለ ነገር የሚናገሩት የሀገሩን ሰላም ማናጋት የሚፈለጉ አሉባልተኞች ናቸው” ይላል።

በሌላ በኩል ፍሪደም ሃውስ የተባለው ዓለም አቀፍ የዴሞክራሲ ሐሳቦች አራማጅ ተቋም በኢትዮጵያ የተፈጠረውን ሁኔታ አስመልክቶ፤ “የኢትዮጵያ መንግሥት ትክክለኛ የሀብት ክፍፍል እና ግልጽ የሆነ መንግሥት እንዲኖር በጠየቁ ዜጎች ላይ የወሰደው ገዳይ እርምጃ እንዲያቆም እንጠይቃለን” ሲል መገለጫ አውጥቷል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በበኩሉ ባወጣው በኦሮሚያ እና በአማራ ክልል በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በፖሊስ ጣቢያ፣ መከላከያ ማሰልጠኛ ጣቢያ ጨምሮ ወዳልታወቁ ማሰሪያ ቦታዎች ተወስደው ታሥረዋል ካለ በኋላ በተቃውሞ ላይ በነበሩበት ወቅት የታሰሩ በሙሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ይዳምጡ።

የኢትዮጵያ ውሎ
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:26 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


XS
SM
MD
LG