በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአነስተኛ ባለይዞታውን ገበሬ የእሴት ሰንሠለት ማጠናከር


ገበያ
ገበያ

የአነስተኛ ባለይዞታ ገበሬዎችን አቅም ለማሣደግና የገበያ አቅርቦታቸውን ለማሻሻል በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ የተነጋገረ ዓለም አቀፍ ስብሰባ ባለፈው ሣምንት አዲስ አበባ ላይ ተካሂዷል፡፡
please wait

No media source currently available

0:00 0:14:19 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ዓለምአቀፍ የግብርናና የገጠር ልማት ትብብር ድርጅት
ዓለምአቀፍ የግብርናና የገጠር ልማት ትብብር ድርጅት


ስብሰባውን ያዘጋጀው ከሰባ በላይ በሚሆኑ ሃገሮች ውስጥ የሚንቀሣቀሰው ዓለምአቀፍ የግብርናና የገጠር ልማት ትብብር ድርጅት ነው፡፡
አቶ ሚካኤል ኃይሉ፤ የዓለምአቀፍ የግብርናና የገጠር ልማት ትብብር ድርጅት ዋና ዳይሬክተር
አቶ ሚካኤል ኃይሉ፤ የዓለምአቀፍ የግብርናና የገጠር ልማት ትብብር ድርጅት ዋና ዳይሬክተር


ዋና ፅሕፈት ቤታቸው ሆላንድ የሆነውን የድርጅቱን ዋና ዳይሬክተርና ስብሰባውን የጠሩትን አቶ ሚካኤል ኃይሉን ሰሎሞን አባተ አነጋግሯቸው ስለድርጅታቸውና ስለስብሰባው ምንነት አስረድተዋል፡፡

በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ እንኳን ሰፊ የገበያ ፍላጎት እንዳለ አቶ ሚካኤል ጠቁመው ድርጅታቸውም የየሃገሩን ገበሬ የማቅረብ አቅም የእሴት ሠንሰለቱን በማጠናከር ለማጎልበት እንደሚሠራ አመልክተዋል፡፡

ከሰባ በላይ ከሚሆኑ የአፍሪካ የፓሲፊክ እና የካሪቢያን ሃገሮች የተሰበሰቡት ከአምስት በላይ የአዲስ አበባው ጉባዔ ተሣታፊዎች የልምድ ልውውጥ ማድረጋቸውንና የተለያዩ ግብርናና ገበያ ነክ ፕሮጀክቶችን መጎብኘታቸውን አቶ ሚካኤል ገልፀዋል፡፡

ቃለ ምልልሱን ያዳምጡ

የኢትዮጵያ ገጠር
የኢትዮጵያ ገጠር
XS
SM
MD
LG