በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ኮቪድ-19 በፍጥነት እየተዛመተ ነው" የዓለም የጤና ድርጅት


የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም
የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም

የፊት ጭምብል መጠቀም ወይስ አለመጠቀም ዛሬ አሚሪካውያንን የከፋፈፈለ ጉዳይ ሆኗል

ፊታቸውን አፍና አፍንጫቸውን በጭንብል ሳይሸፈኑ ደጅ ዝር የማይሉ አሉ ሳይሸፈኑ የሚዘዋወሩም አሉ

ጉዳዩ አብዝቶ ያሳሰባቸው የቴክሳስ ክፍለ ግዛት ዘጠኝ ከተሞች ከንቲባዎች ለነዋሪዎቻቸው በጻፉት ደብዳቤ እባካችሁ ያለጭንብል አትውጡ ብለው አጥበቀው መማጸናቸውን ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ዘግቧል

"ቫይረሱ መዛመቱን ቀጥሏል ፥ የህመምተኛው ብዛት ከሆስፒታሎች ዓቅም በላይ እየሆነ ነው፤ ሃቁን ልንነግራችሁ እንጂ ልናስፈራራችሁ ፈልገን አይደለም፤ ቫይረሱ እኛ ቸል ስላልነው አይወገድም" ሲሉ ከንቲባዎቹ መማጸናቸውን ፖስት ዘግቧል

በሌላ የኮቪድ አስራ ዘጠኝ ዜና ዓለም አቀፉ ወረርሽኝ በፍጥነት እየተዛመተ መሆኑን የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም አስገንዝበዋል

ከትናንት በስቲያ ሃሙስ ብቻ በዓለም ዙሪያ የተመዘገበው የአዲስ የቫይረሱ ተያዦች አሃዝ ከአንድ መቶ ሃምሳ ሽህ በላይ መሆኑን የገለጹት ዶክተር ቴድሮስ ይህም ኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከጀመረበት ከታህሳስ ወር ወዲህ በአንድ ቀን ከተገኙት ሁሉ ትልቁ መሆኑን አሳስበዋል

XS
SM
MD
LG