በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮሮናቫይረስ ክትባት መድሃኒት መጀመሩን 'ሞደርና' የተባለ ኩባንያ አስታወቀ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ሞደርና የተባለው የባዮቴክኖሎጂ ኩባንያ፣ አንድ አዲስ የኮሮናቫይረስ ክትባት መድሃኒት፣ በ30,000 ጎልማሶች ላይ ሙከራ መጀመሩን አስታውቋል።

ከብሄራዊ የአለርጂና የተላላፊ በሽታዎች ተቋም ጋር በመተባበር፣ ሙከራው ዛሬ የተጀመረው፣ በሳቫና ጆርጂያ መሆኑን ኩባንያው አስታውቋል። ሳቫና በሀገቱ ዙሪያ ካሉት፣ በርካታ የሙከራ ቦታዎች፣ አንዱ ነው ተብሏል።

የቫይረሱ ክትባት እንዲሞከርባቸው ከቀረቡት ስዎች ግማሾቹ፣ እውነተኛው ክትባት እንደሚሰጣቸው፣ የተቀሩት ግን የውሸት ክትባት እንደሚከተቡ፣ አሶሼተድ ፕሬስ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።

ሞደርና እስካሁን ባለው ጊዜ ባደረጋቸው፣ የክትባቱ መድሃኒት ሙከራዎች፣ ጠንካራ የመከላከል ምላሽ ማሳየቱን፣ በያዝነው ወር ቀደም ሲል አስታውቋል። ድካምን፣ ራስ ምታትን፣ የብርድ-ብርድንና የሰውነት መቀጥቀጥን የመሳሰሉት፣ ቀለል ያሉ የጎንዮሽ ስሜቶች ማስከተሉ ተጠቅሷል።

ሁለት ሌሎች የሙከራ ክትባቶችም፣ በሰዎች ላይ ተሞክረው ጠንካራ የመከለከል ምላሽ ማሳየታቸውን፣ በያዝነው ወር ዘ - ላንሰት በተባለ፣ ስለ ህክምና ጉዳይ የሚዘግብ፣ የብሪታንያ መጽሄት ላይ የወጣ ጥናት ጠቁሟል።

አንደኛው የክትባት መድሃኒት የተሰራው፣ በብሪታንያው ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲና በብሪታያና የስዊድን መድሀኒት ኩባንያ /AstraZeneca/ ትብብር ሲሆን፣ ሁለተኛው የክትባት መድሃኒት ደግሞ /Can Sino Biologics/ በተባለው፣ የቻይና የባዮቴክኖሎጂ ኩባንያ መሆኑ ታውቋል።

XS
SM
MD
LG