በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና ውስጥ የኮቪድ-19 ተጋላጮች ቁጥር ማሻቀቡን ቀጥሏል


ወደ ጊዜያዊ የኮሮናቫይረስ ሆስፒታል ለመቀየር ሰራተኞች ቻይና በቻንግቹን፣ ጂሊን ግዛት ውስጥ በሚገኝ ስታዲየም አልጋዎችን እያዘጋጁ እአአ መጋቢት 12/2022
ወደ ጊዜያዊ የኮሮናቫይረስ ሆስፒታል ለመቀየር ሰራተኞች ቻይና በቻንግቹን፣ ጂሊን ግዛት ውስጥ በሚገኝ ስታዲየም አልጋዎችን እያዘጋጁ እአአ መጋቢት 12/2022

ቻይና ውስጥ የኮሮናቫይረስ አዲስ ተጋላጮች ቁጥር ከእጥፍ በላይ መጨመሩ ተገለጠ። ወረርሽኙ ከሁለት ዓመታት በፊት ከተቀሰቀሰ ወዲህ ከፍተኛው የሆነውን የቫይረሱን ሥርጭት ለመቆጣጠር በመታገል ላይ ነች።

ብሂራዊ የጤና ኮሚሽኑ እንዳስታወቀው ባለፈው የሃያ አራት ሰዓት ጊዜ ውስጥ ብቻ 3507 አዲስ ተያዦች የተመዘገቡ ሲሆን በንፅፅር ትናንት የተመዘገቡት 1337 ነበሩ።

በቫይረሱ መዛመት የተነሳ በሰሜን ምስራቅ የሃገሪቱ አካባቢዎች አዳዲስ ገደቦች ወጥተዋል።

በደቡብ ምስራቅዋ ጉዋንዶንግ ክፍለ ሀገርም የሀገሪቱ የቴክኖሎጂ ኩባኒያዎች የሌሎችም ኢንዱስትሪዎች መናኽሪያ በሆነችው ሺንዜን ከተማ ባለሥልጣናት የቫይረሱን ሥርጭት ለመቆጣጠር የምርት እንቅስቃሲዎችን በሙሉ አዘግተዋል።

አዲስ የቫይረሱ ተያዦች እየበረከቱ ወዳሉባት የንግዷ ከተማ ወደሻንግሃይ ከተማ የሚያመሩ የሃገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ በረራዎች ሌሎች ከተሞች እንዲያርፉ ተደርጓል።

የቻይና መንግሥት ኮሮናቫይረስን ከሀገሪቱ ሙሉ በሙሉ ለማስወገድ ዚሮ ኮቪድ-19 ሲል የጠራውን ዕቅድ ያወጣ ቢሆንም በእጅጉ ተላላፊ በሆነው የቫይረሱ ዝርያ በኦሚክሮን ምክንያት ሥርጭቱ እየጨመረ መጥቷል።

XS
SM
MD
LG