በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዶ/ር ቴድሮስ ዓለም በኮቪድ-19 ወሳኝ ወቅት ላይ ይገኛል አሉ


ፎቶ ፋይል፦ የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም
ፎቶ ፋይል፦ የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም

የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም፣ ዛሬ ሰኞ በሰጡት መግለጫ፣ ሦስተኛ ዓመቱን በያዘው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የተጋለጡት የዓለም አገራት፣ ወረርሽኙን ለማስቆም ወደ አንድነት መምጣት ይኖርባቸዋል ሲሉ አሳሰቡ፡፡

ዳይሬክተሩ ጀርመን ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ

“በጣም ወሳኝ ወቅት ላይ እንገኛለን፣ ጭንቀትና ቸልተኝነት አሁንም ወደፊት እንዲጎትተን ማድረግ የለብንም” ብለዋል፡፡

በአውሮፓ የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ሄንሪ ክለግ የኦሚክሮን ቫይረስ በአውሮፓ በመጋቢት ወር 60 ከመቶ የሚሆነውን ሰው ሊያጠቃ እንደሚችል ተንብየዋል፡፡

ይሁን እንጂ ከዚያ በኋላ ብዙ ሰው የተከተበ ወይም ከቫይረሱ ጋር የተላመደ በመሆኑ ወደ ማብቂያው ማምራቱ መልካም ዜና መሆኑን ዳይሬክተሩ ክለግ ገልጸዋል፡፡

በዩናትይትድ ስቴትስ የተላላፊ በሽታዎች ከፍተኛ ባለሙያ ዶ/ር አንተኒ ፋውቺም ባላፈው እሁድ በሰጡት መግለጫ በጣም እንዳያዘናጋን እንጂ ነገሮች እየተሻሻሉ ነው ብለው መናገራቸው ተሰምቷል፡፡

XS
SM
MD
LG