በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ ለኮሮና ቫይረስ የተጋለጡ ተጨማሪ 707 ሰዎች ተገኙ፤ የ 28 ሰዎች ህይወት አለፈ


 ዶክተር ሊያ ታደሰ
ዶክተር ሊያ ታደሰ

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 7 ሺህ 607 የላብራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 707 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸውና የ 28 ሰዎች ህይወት ማለፉን የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

በዚህም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 18 ሺህ 706 ደርሷል።

እንዲሁም የተጨማሪ የ28 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 310 መድረሱም ታውቋል።

ዛሬ ከተገኙት የኮሮና ቫይረስ ተጋላጮች ውስጥ አራት መቶ ሰማኒያ ስምንቱ በአዲስ አበባ ፤ ዘጠና አምስት በኦሮምያ፤ ሰላሳ አንድ በትግራይ፤ ሃያ ዘጠኝ በደቡብ ክልል አስራ አምስት በሶማሌ፤ ስምንት በአማራ ፤ሰባት በአፋር ፤ ስድስት በጋምቤላ፤ አራት በድሬደዋ ሶስት በሃረሪ እና ሶስት በቤንሻንጉል ጉምዝ የተገኙ መሆናቸውን የሚኒስቴሩ ዕለታዊ መረጃ ዘርዝሯል

በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 406 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን በዚህም በአጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 7 ሺህ 6 01 ደርሷል፡፡

XS
SM
MD
LG