በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአፍሪካ የኮቪድ 19 ክትባት አሰጣጥ ቀንሷል


በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ለተከተቡ ሰዎች የምስክር ወረቀት ሲዘጋጅ፡፡ እኤአ ህዳር 15 2021
በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ለተከተቡ ሰዎች የምስክር ወረቀት ሲዘጋጅ፡፡ እኤአ ህዳር 15 2021

በአፍሪካ የጤና ባለሥልጣናት በአህጉሪቱ የኮቪድ 19 ክትባት ስርጭት እየቀነሰ መምጣቱ ወረርሽኙን የማቆሙን ጥረት አሳሳቢ አድርጎታል ይላሉ፡፡ በዓለም ፍትሃዊ ተደራሽነት እንዲኖር ሲባል በኮቫክስ አማካይነት ወደ አህጉሪቱ እየገቡ ያሉትን የክትባት መድሃኒቶችንም አፍሪካውያን በተቻለ መጠን እንዲከተቡ ጥሪያቸውን እያስተላለፉ ነው፡፡

በአፍሪካ የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይም በዚህ የበዓል ሰሞን አፍሪካውያን የሚያደርጉትን ጥንቃቄ መቀነሳቸውን በመቃወም አስጠንቅቀዋል፡፡

ትናንት ሀሙስ በበይነ መረብ ላይ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫቸው የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠሪያና መከላከል ማዕከል ዳይሬክተር ጆን ኒከንጋሶንግ በአፍሪካ የኮቪድ 19 ክትባት ስርጭት መቀነሱን ተናግረው ይህን አክለዋል፦

“ወደ አፍሪካ ከደረሱ የክትባት መድሃኒቶች ውስጥ ጥቅም ላይ የዋሉት 55 ከመቶ ብቻ ናቸው፡፡ ይህ በስርጭት ምክንያት መሆኑ በእውነት ተቀባይነት የለውም፡፡ ሰዎች መከተብ ከፈለጉ መከተብ መቻል አለባቸው፡፡ አህጉሪቱ ውስጥ ክትባቱን ማግኘት የሚችሉ ሰዎች ሁሉ ክትባቶቻቸውን ሄደው እንዲወስዱ ጥሪ እያደረግን ነው፡፡ ራሳችንን መከላከል የምንችልበት ብቸኛው መንገድ ይህ ብቻ ነው፡፡

የአህጉሪቱ የጤና ማዕከል ክትባቱ የቀነሰው ሰዎች መከተብ ባለመፈልጋቸው ሳይሆን ክትባቶቹን ከአውሮፕላን ማረፊያዎች ወደ የሰዎቹ ክንድ ላይ ማድረስ ባለመቻሉ መሆኑን ይናገራሉ፡፡

እስከዛሬ አፍሪካ ያስከተበቸው ከህዝቧ 10 ከመቶ የሆነውን ብቻ ነው፡፡በተባበሩት መንግስታት ለመካከለኛና አንስተኛ ገቢ ላላቸው አገሮች እንዲዳረስ ከታሰበው ዓለም አቀፉ የኮቫክስ ስርጭት አፍሪካ የተቀበለችው 330 ሚሊዮን የክትባት መድሃኒቶችን መሆኑም ተነግሯል፡፡ ይሁን እንጂ የአፍሪካ ህዝብ ብዛት 1.3 ቢሊዮን መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ሪቻርድ ሚሂጎ በአፍሪካ የዓለም ጤና ድርጅት የተፈጥሯዊ መከላከልና የክትባት መድሃኒት ምርት ፕሮግራም ድሬክተር ናቸው፡፡ እንዲህ ይላሉ

“አሁን ተጨማሪ ክትባት ያለን መሆኑ መልካም ዜና ነው፡፡ አሁን አገሮች እየተዘጋጁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ እየሞከርን ነው፡፡ እንዲያውም አሁን የተለያዩ ስትራቴጂዎችን በመከተል እጅግ ለተጎዱት ብቻ ሳይሆን እድሜያቸው ከ12 ዓመትና ከዚያ በላይ ያሉ ህጻናት ሁሉ እንዲከተቡ በሩን ክፍት አድርገዋል፡፡”

ኬንያ የኮቪድ 19 ክትባት ስርጭት የቀነሰባቸው መሆኑን ከተረዱ አገሮች አንዷ ናት፡፡ በዚህ ሳምንት ባለሥልጣኖችዋ ያልተከተቡ ግለሰቦች የመንግሥታዊ አገልግሎት እንዳያገኙ አድርገዋል፡፡

በአፍሪካ የዓለም ጤና ድርጅት ድሬክተር ማትሺዶ ሞኤቲ በታህሳሱ የበዓል ዝግጅት ህዝቡ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት ይላሉ፡፡ ምክንያቱንም ሲያስረዱ

“በደቡባዊ አፍሪካ አገሮች የአዳዲስ ተጋላጮች ቁጥር ከቀደሙት ሳምንታት ጋር ሲነጻጸር ወደ 48 ከመቶ እያደገ መምጣቱን ተመልክተናል፡፡ ለ18 ሳምንታት በቋሚነት እየቀነሰ ከመጣ በኋላ ነው፡፡ ይህ የሆነው በደቡባዊ አፍሪካ አገሮች እየጨመረ በመምጣቱ ነው፡፡ ስለዚህ አሁን ክትባት ዋነኛ መከላከያችን መሆኑን እናውቃለን፡፡ ይሁን እንጂ የበለጸጉ አገሮች ከ60 ከመቶ በላይ ህዝባቸውን ሲያስከትቡ በአፍሪካ ሙሉውን ክትባት የወሰዱት ከ7 ከመቶ ጥቂት ከፍ ያሉት ብቻ ናቸው፡”

ቦትስዋና እና ደቡብ አፍሪካ B.1.1529, የተባለ አዲስ የኮቪድ 19 ዝርያ የተከተሰባቸው ሲሆን ዝርያው በከፍተኛ ደረጃ የሚተለለፍ፣ ክትባትንም መቋቋም የሚችል መሆኑ ታምኖበታል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ዘገባ እንደሚያስረዳው፣ በአፍሪካ 27 ከመቶ የሚሆኑን የጤና ባለሙያዎች ሙሉ ክትባት የወሰዱ ቢሆንም አብዛኞቹ የጤናው ዘርፍ ሠራተኞች ግን ያለምንም መከላከል ለወረርሽኙ የተጋለጡ ናቸው፡፡

በአፍሪካ ከ8.6 ሚሊዮን በላይ የኮረና ቫይረስ ተጋላጮች ሲኖሩ ወደ 221ሺሰዎች በኮቪድ 19 ቫይረስ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG