ደቡብ አፍሪካ ከአሜሪካ፣ ብራዚል፣ ሩሲያና ህንድ ቀጥሎ ኮሮናቫይረስ የጸናባት ሃገር ስትሆን 599,940 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋልጠዋል። ከኮሮናቫይረስ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 497,169 ሲሆን በበሽታው የሞቱ ደግሞ 12,618 መድረሱን የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የኮቪድ-19 መረጃ ማዕከል መረጃ አስታውቋል።