ኒው ዚላንድ የኮሮናቫይረስን ወረርሽኝ በመቆጣጠር በኩል ስኬት በማግኘቷ፣ የሃገሪቱ መሪዎች በመጪው ሳምንት፣ የአካል መራራቅ እንዲኖር የደነገጉትንና ሰዎች እንዳይሰባሰቡ የጣሉትን እገዳሊያነሱ እንደሚችሉ ተገልጿል።
አስቀድሞ ጠንካራ እርምጃ መውሰድ፣ የሚለው ስትራቴጂያችን ሰርቷል ሲሉ፣ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደርን ተናግረዋል።
ሀገሪቱ ከስድስት ሳምንታት በላይ ለሆነ ጊዜ፣ ጥብቅ የመንቀሳቀስ እገዳደንግጋ ከቆየች በኋላ፣ ለ11 ቀናት ያህል አዲስ የቫይረሱ በሽተኞች አልተገኙባትም። የሀገሪቱ የካቢኔ ሚኒስትሮች፣ድንበሮች እንደተዘጉ ሆነው፣ የቁጥጥር ማላላት ለመጀመር በመጪው ሰኞ ይወስናሉ።
በእንደዚህ አይነት ፍጥነት ወደ መደበኛ አሰራር ለመመለስ፣ በዓለም የመጀመሪያዎቹ ከሆኑት ሀገሮች እንመደባለን ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሯ።