ዋሺንግተን ዲሲ —
ህንድ ዛሬ ከ1,000 በላይ የሚሆኑ ሰዎች፣ በኮሮናቫይረስ መሞታቸውን አስታውቃለች። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከገባበት ጊዜ አንስቶ፣ የተጠቀሰውን ቁጥር የሚያክል ብዛት ያላቸው ሰዋች ሲሞቱባት የመጀመሪያ መሆኑ ተገልጿል።
በአዲሱ የወረርሽኙ አሃዝ መሰረት፣ ህንድ ውስጥ 44,386 ሰዎች በኮቪድ-19 ሞተዋል። ከዩናይትድ ስቴትስ፣ ብራዚል፣ ሜክሲኮና ብሪታንያ ቀጥሎ፣ ከዓለም አምስተኛዋ ሆናለች።
ህንድ ለተከታታይ ሥድስት ቀናት፣ ከዓለም የበዙ አዲስ የቫይረሱ በሽተኞች፣ እየተገኙ መሆናቸውን አስታውቃለች። ዛሬ 62,000 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ማግኘቷን ገልጻለች።
ህንድ ውስጥ ለኮሮናቫይረስ የተጋለጡ ሰዎች ቁጥር 2,215,074 መድረሱን፣ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 1,535,743 መሆናቸውን በኮቪድ-19 የሞቱ 44,386 መድረሳቸውን የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የኮቪድ-19 መረጃ ማዕከል መረጃ አስታውቋል።