በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 በዩናይትድ ስቴትስ


መራጮች ወደ ምርጫ ጣቢያ ሲገቡ የኮሮናቫይረስ ምርመራ እየተደረገላቸው ሚዙሪ
መራጮች ወደ ምርጫ ጣቢያ ሲገቡ የኮሮናቫይረስ ምርመራ እየተደረገላቸው ሚዙሪ

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ትናንት ሰዎች ለምርጫ በተሰለፉበት ሁኔታ፣ ሀገሪቱ በአንድ ቅን ውስጥ፣ የበዙ በኮቪድ-19 የተያዙ ስዎች ማግኘትዋን አስታውቃለች።

የኮሮናቫይረስን ጉዳይ የሚከታተለው፣ የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ባወጣው አሃዝ መሰረት፣ በትናንቱ የምርጫ ዕለት፣ 91,530 የሚሆኑ ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተይዘዋል። 1,130 የሚሆኑት ደግሞ ለሞት ተዳርገዋል። በተጨማሪም ትናንት ብቻ፣ ከ50,000 በላይ የቫይረሱ በሽተኞ ሆስፒታል ገብተዋል።

በፕሬዚዳንታዊ የምርጫ ውድድር፣ አብይ ሚና የተጫወቱት ሚችገን፤ ኦሃዮና ፔንስልቬንያ ክፍላተ-ግዛት፣ በትናንቱ ዕለት ብቻ፣ የበዙ የቫይረሱ በሽተኞች ማግኘታቸውን ገልጸዋል።

በአጠቃላይ ከ20 በላይ የሚሆኑ ክፍላተ-ግዛት፣ ከዚህ ቀደም ከታዩት የአንዳንድ ሳምንት ጊዜ፣ የቫይረሱ በሽተኞች ብዛት የላቀ ቁጥር፣ ባለፈው ሳምንት እንደተከሰተ አስታውቀዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚታየው፣ የኮሮናቫይረስ መዛመት ሁኔታ፣ የሃገሪቱን መላ የስፖርት ዓለምን እንደጎዳ ተገልጿል።

በሀገሪቱ ከ9.3 ሚሊዮን በላይ የቫይረሱ በሽተኞች ያሉ ሲሆን፣ ከዓለም ቀዳሚ ቦታ ማያዟ ቀጥሏል። በዓለም ደራጃ 47.4 ሚሊዮን የኮቪድ-19 በሽተኞች እንዳሉ ታውቋል። የሞቱት ደግሞ 232,627 መሆናቸው ተገልጿል።

ፈረንሳይም ትናንት 854 አዲስ የቫይረሱ በሽተኞች ማግኘቷን ገልጻለች። ካለፈው ሚያዝያ ወር አንስቶ፣ የበዛ ቁጥር እንደሆነ፣ ሮይተርስ የዜን አገልግሎት ዘግቧል።

በኮቪድ በሽተኞች ብዛት፣ ከዓለም ሁለተኛ በሆነችው ህንድ ደግሞ፣ ከ8.3 ሚሊዮን በላይ የቫይረሱ በሽተኞች እንዳሉ ታውቋል። ባለፉት 24 ሰዓታታ ውስጥ ከ46,000 በላይ አዲስ በሽተኞች መኖራቸው ተገልጿል።

XS
SM
MD
LG