No media source currently available
የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ክስ ቀርቦባቸው ከነበሩ ተጠርጣሪዎች መካከል የ63ቱን ተከሳሾች ክስ እንዲቋረጥ ጉዳያቸውን ለሚመለከተው ፍርድ ቤቶች ማመልክቱን አስታወቀ። በከፍተኛ ወንጀሎች ተጠርጥረው የተከሰሱ ግለሰቦች ክስ ግን እንደማይቋረጥ ጨምሮ ገልጿል። ጠቅላይ ዐቃቢ ህግ አያይዞም የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ይበልጥ ተጠናክረን በመሥራት ላይ ነን ብሏል።