በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እነአቶ አምኃ ዳኘው እና አምስት ሰዎች ጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባቸው


እነአቶ አምኃ ዳኘው እና አምስት ሰዎች ጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባቸው
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:03 0:00

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አምኃ ዳኘውን ጨምሮ፣ በረዳት ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው ሥር፣ የክሥ መዝገብ የተከፈተባቸው ስድስት ግለሰቦች፣ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበው፣ የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ተሰጠባቸው።

ፖሊስ ግለሰቦቹን፣ ዐዲስ አበባንና ባሕር ዳርን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች፣ በኅቡእ አደረጃጀት ሁከት እና ብጥብጥ በማሥነሳት ወንጀል እንደጠረጠራቸው ለፍርድ ቤቱ መግለጹን ጠበቃው ተናግረዋል።

በክሥ መዝገቡ የተካተቱት በአጠቃላይ ስድስት ግለሰቦች እንደኾኑና አምስቱ፣ በኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም፣ በሐረምያ እና በወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች፣ በመምህርነት በመሥራት ላይ የሚገኙት፥ ፕሮፌሰር ማዕርጉ ቢበይን፣ ረዳት ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው፣ ኄኖክ ዐዲስ፣ ዶር. መሠረት ወርቁ እና ዶር. ወንድወሰን አሰፋ እንደሚገኙበት ተገልጿል፡፡

ከጠበቆቻቸው አንዱ የኾኑት፣ የሕግ አማካሪ እና ጠበቃ ሰሎሞን ገዛኸኝ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ሲገልጹ፣ ከስድስቱ ተጠርጣሪዎች አንዱ የኾኑት ፕሮፌሰር ማዕርጉ ቢበይን፣ በ30 ሺሕ ብር ዋስ እንዲፈቱ ተወስኗል፤ ብለዋል።

ተጠርጣሪዎቹ፣ ባለፈው ዓርብ፣ መጋቢት 22፣ 2015 ዓ.ም. እኩለ ሌሊት አካባቢ መያዛቸውን የተናገሩት ጠበቃው፣ ፍርድ ቤቱ፣ የ14 ቀናት ጊዜ ቀጠሮ በሰጠበት በትላትናው ዕለት፣ በችሎት ቀርበው ክርክር መደረጉንና ፖሊስ በምን ወንጀል እንደጠረጠራቸው ማስረዳቱን አክለው ገልጸዋል።

አቶ ሰሎሞን ገዛኸኝ፣ ስለ ጉዳዩ የሰጡትን ማብራሪያ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG