በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሳልሳይ ወያነ ትግራይ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባል ፍ/ቤት ቀረቡ


የሳልሳይ ወያነ ትግራይ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባል ፍ/ቤት ቀረቡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:35 0:00

የሳልሳይ ወያነ ትግራይ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባል አቶ ሃይሉ ከበደ ፍርድ ቤት ቀረቡ።

የሳልሳይ ወያነ ትግራይ ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ሐላፊ አቶ ሀይሉ ከበደ በፌዴራሉ መንግሥት በአሸባሪነት ከተፈረጀው ህወሓት ጋር ሚስጥራዊ ግንኙነት በመፍጠር ወንጀል ተጠርጥረው በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡ ፖሊስ አቶ ሃይሉ ከበደ በተጠረጠሩበት ወንጀል ዙርያ የምርመራ ሥራውን በሰውና በሰነድ ማስረጃ ለማጣራት እንዲችል የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎትን ጠይቋል፡፡ የተጠርጣሪ ጠበቃ በበኩላቸው በተጠርጣሪው አያያዝ ዙርያ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል፡፡ ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን ቀጠሮ በመቃወምም ተጠርጣው ዋስትና እንዲፈቀድላቸው ተከራክረዋል፡፡ ፍ/ቤቱ ደግሞ መቃወሚያውን ውድቅ በማድረግ ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ ለመስከረም 5 ቀን 2014 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

XS
SM
MD
LG