በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቻይና አዲስ የኮሮናቫይረስ ተያዦች ቁጥር ቀንሷል


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

አዲስ የኮሮናቫይረስ ተያዦች ቁጥር ከምንጊዜውም ይበልጥ ቀንሷል ስትል ቻይና ተናገረች። ወረርሺኙ ከሁለት ወራት በላይ በፊት ከተቀሰቀሰ ወዲህ ቻይና ውስጥ ከሁለት ሺህ የሚበልጥ ህዝብ ገድሏል።

የሃገሪቱ የብሄራዊ ጤና ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ እንዳለው በትናንትናው ዕለት የተመዘገቡት አዲስ የኮሮናቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር 394 ብቻ ነበር። ለንጽጽር ማክሰኞ ዕለት 1749 ተመዝግቧል።

ተጨማሪ 114 ሰዎች በበሽታው ምክንያት በመሞታቸው እስካሁን የሞቱት ሰዎች ቁጥር 2118 ደርሷል። አጠቃላይ የተረጋገጡ የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር ደግሞ 74,576 መድረሱ ተጠቁሟል።

በዘገባዎች መሰረት ከቻይና ውጭ በቫይረሱ ሳቢያ ቢያንስ አስራ አንድ ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል። አንድ በደቡብ ኮሪያ ሁለት ሰዎች በኢራን በተጨማሪም ከጃፓን ዮኮሃማ ወደብ እንዳትንቀሳቀስ የተደረገችው ዳያመንድ ፕሪንሰስ በተባለችው መዝናኛ መርከብ ላይ የነበሩ በሰማንያዎቹ ዕድሜ የነበሩ ባልና ሚስት ይገኙባቸዋል።

ቻይና መጋለጣቸው የተረጋገጠ አዲስ የኮሮና ተጠቂዎች ቁጥር ቀንሷል ብትልም የዓለም የጤና ድርጅት ሰዎች የባሰው ጊዜ አልፉል፣ ብለው ከመዘናጋት እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG