በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአየር ንብረቱ ዩናይትድ ስቴትስና ቻይና የጋራ ሥምምነት አወጡ


በአየር ንብረቱ ዩናይትድ ስቴትስና ቻይና የጋራ ስምምነት አወጡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:44 0:00

በአየር ንብረቱ ዩናይትድ ስቴትስና ቻይና የጋራ ስምምነት አወጡ

ዩናይትድስ ስቴትስና ቻይና በሚቀጥለው አስር ዓመት ውስጥ የዓለም ሙቀት መጠንን ከ2 ዲግሪ ሲልሽየስ በታች ለማድረግ የሚያስችለውን የረጀም ጊዜ የስትራቴጂ እቅድ ለማውጣት ትናንት ረቡዕ በጋራ ስምምነት ያወጡት መግለጫ የCOP26 የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ታዳሚዎችን አስደንቋል፡፡

የስምምነቱ ዜና የመጣው፣ የዓለም አየር ሙቀትን ለመቀነስ የሚቻልበትን ስምምነት ለማምጣት፣ የሚደረገው ጥረት የመጨረሻው ሰዓት ላይ በደረሰበት ጊዜ ነው፡፡

ቻይናና ዩናይትድ ስቴትስ የአየር ንብረትን በመበከል የሚታወቁ ሁለቱ ትላልቅ አገሮች ናቸው፡፡

ሁለቱ አገሮች የሚወስዱት ውሳኔ የወደፊቱን የአየር ንብረት ለውጥ ለመወሰን ይረዳል፡፡

ስለሆነም ሁለቱ አገሮች፣ በጋራ ያወጡት መግለጫ የCOP26 የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ታዳሚዎችን ድጋፍ አግኝቷል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የአየር ንብረት ልዩ ልኡክ ጆን ኬሪ እንዲህ ይላሉ

“ ዩናይትድ ስቴትስና ቻይና የሚለያዩባቸውን ነገሮች አላጡም፡፡ የአየር ንብረት ለውጥን በመሚለከት ግን ሥራው እንዲሰራ ከተፈለገ ያላቸው ብቸኛ መንገድ በትብብር መስራት ብቻ ነው፡፡ እውነቱን እንነጋገር ከተባለ ይህ አስተዋይነት አይደለም፡፡ ይሄ ሳይንስ ነው፡፡ እንድጓዝበት የሚያስፈልገውን መንገድ የሚነግረን ሂሳብና ፊዚክስ ነው፡፡”

የቻይና የአየር ንብረት ዋነኛ ተደራዳሪ ዚ ዜኑሃም እንዲህ ብለዋል

“የአየር ንብረት ለውጥን በሚመለከት፣ በዩናትድ ስቴትስና በቻይና መካከል ከሚያለያዩን ነገሮች ይልቅ ሊደረጉ የሚገባቸው በርካታ ስምምነቶች አሉ ፣ ለጋራ ትብብራችን ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዲያደርጉም መጠቀም ይቻላል;”

በሁለቱ አገሮች መካከል፣ የስምምነት ቃል ከተገባባቸው ውስጥ፣ የሜይቴን ጋዝ ልቀትን፣ ህገወጥ የደን ጭፈጨፋን፣ የታዳሽ ኃይል ውጤቶችን ማጠናከርን፣ ለደሀ አገሮች የሚሰጠውን የፋይናንስ እርዳታ ማፋጠን ይገኙበታል፡፡

ይሁን እንጂ የስምምነቱ መግለጫ የተለየ ቀን እና ግብን ለይቶ አላስቀመጠም፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬስ፣ ከስምምነቱን በኋላ ባስተላለፉት የትዊት መልዕክት

“የአየር ንብረት ለውጡን ቀውስ ለማስወገድ ዓለም አቀፍ ትብብርና አጋርነት ያስፈልጋል፣ ይህ ወደ ትክክለኛው አቅጣጫ ለማምራት አስፈላጊ እምርጃ ነው” ብለዋል፡፡

በአየር ንብረት ዙሪያ፣ የጉባኤው ተሳታፊ አገሮች፣ የዓለም የሙቀጥ መጠንን ከ1.5 ዲግሪ ሴልሺየስ እንዳይበልጥ ለማድረግ የሚደርሱበትን የመጨረሻ ስምምነት ውሳኔ፣ እስከ አርብ ድረስ አትመው ለማውጣት ዝግጅት ላይ በሚገኙበት በዚህ ወቅት፣ በዩናይትድ ስቴትስና ቻይና የተደረሰበት ስምምነት ሂደቱን እንዲቀላጠፍ እንደሚያደርገው ተነግሯል፡፡

ዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ጉባኤ፣ አዘጋጅ አገር መሪ የሆኑት፣ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆነሰን፣ የጉባኤው ተሳታፊዎች ይህን አጋጣሚ እንዲጠቀሙበት በማሳሰብ እንዲህ ብለዋል

“ዛሬ ነገሮች እጅግ አስቸጋሪ ሆነው እያገኘናቸው ነው፡፡ ይሁን እንጂ ግን አይቻሉም ማለት አይደለም፡፡ የዓለም የሙቀት መጠንን ከ1.5 ዲግሪ ሲልሺየስ በታች ማድረግ አንችልም ማለት አይደለም፡፡”

በጉባኤ ተስታፊዎች ዘንድ፣ የአየር ንብረት ቀውሱን ለመቋቋም፣ የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉና ፣ኢኮኖሚያቸውን ከካርቦን ልቀት ውጭ እንዲገነቡ ማድረግ የሚቻልበትም መንገድ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡

እኤአ በ2019 በተገባው ቃል መስረት፣ የበለጸጉ አገሮች ለታዳጊ አገሮች ምን ያህል ገንዘብ መስጠት ይገባቸዋል በሚለው ጉዳይ ላይ፣ ተሳታፊዎቹ እየተደራደሩ ነው፡፡

ትናንት ረቡእ ታትሞ የወጣው የመጀመሪያ ረቂቅ አገሮች፣ የሚያደርሱትን ልቀት እኤአ በ2002 መጨረሻ ላይ የሚቀንሱበትን መንገድ መከለስና ማጠናከር እንዳለባቸው ያሳስባል፡፡ የበለጸጉ አገሮች ለድሆቹ አገሮች በየዓመቱ ለመገለስ ቃል ከገቡት አንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ እንዲሄዱ ያሳስባል፡፡

መንግስታት የከሰልና የተፈጥሮ የጋዝ ምርቶቻቸውን እንዲቀንሱም ያዛል፡፡ ይሁን እንጂ ለአፈጻጸሙ የተወሰኑ ቀነ ገደቦችን አላመለከተም፡፡

ጀኒፈር ሞርጋን የግሪን ፒስ ኢንተርናሽናል ሥራ አስጸሚ ናቸው፡፡ እንዲህ ይላሉ

“ አገሮች እንዲያውም ተመልሰው መጥተው ያስቀመጧቸውን ግቦችና እምርጃዎቻቸውን ማጠናከር ይኖርባቸዋል፡፡ ያ አንድ ነገር ነው፡፡ የስምምነቱ ሰነድ የከሰልና የተፈጥሮ ጋዞችን የሚያመነጩ ሁሉ እንደሚቋረጡ ይገልጻል፡፡ እርግጥ ነው በምን ቀንና መች ሊወገዱ እንደሚገባ መቀመጥ ይኖርባታል፡፡ ይሁን እንጂ በሰነዱ መቀመጣቸው በራሱ አንድ ነገር ነው፡፡”

ቻይናና ዩናይትድ ስቴትስ በጋራ ያወጡት መግለጫ፣ ለጉባኤ ተጨማሪ ግብአት ሆኗል፡፡

ቀሪዎቹ ሰዓታት፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ፣ እጅግ አደገኛ የሆነውን የዓለም የሙቀት መጠንን ለመቀነስ መስማማቱን የሚያሳይበት ይሆናሉ፡፡

XS
SM
MD
LG