በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ መሪዎች የበለጸጉ አገሮች የገቡትን 100 ቢሊዮን ዶላር ቃል እንዲጠብቁ ጠየቁ


የጋና ፕሬዝዳንት ናና አዶ፣ ዳንክዋ አኩፎ አዶ
የጋና ፕሬዝዳንት ናና አዶ፣ ዳንክዋ አኩፎ አዶ

የአየር ንብረት ጉባኤው ተጠናቀቀ

በግላስኮ ስኮትላንድ ዓለም አቀፍ የCOP26 የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ የተገኙት የአፍሪካ አገሮች፣ የገጠማቸውን የአየር ንብረት ለውጥ ለመቋቋም እንዲያግዛቸው በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮችን እለንግሳለን ብለው የገቡትን አላካበሩም ሲሉ የበለጸጉ አገሮችን ወቀሱ፡፡

በዓለም የበለጸጉ አገሮች የተባሉት የቡድን 20 አባል አገራት 80 ከመቶ ለሆነው የአረንጓዴ ጋዝ ልቀት ተጠያቂ ቢሆኑም ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ከፍተኛውን የአየር ንብረት ቀውስ ገፈት ቀማሾቹ ድሆቹ አገሮች በተለይም አፍሪካ ውስጥ ያሉት መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡

የበለጸጉ አገሮች እኤአ በ2009፣ በአየር ንብረት ቀውስ ለተጎዱ ታዳጊ አገሮች በየዓመቱ የ100 ቢሊዮን ዶላር ሊሰጡ ቃል የገቡ ቢሆንም፣ እንደ ግብ የተቀመጠው ቀን፣ ዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ጉባኤ እስከሚደረግበት እኤአ 2023 ድረስ የተገፋ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ይህ ትናንት ማክሰኞ በጉባኤው ላይ የነበሩትን የአፍሪካ መሪዎች አስቆጥቷል፡፡ ቁጣቸውን ከገለጹት መካከል የጋናው ፕሬዝዳንት ናና አዶ፣ ዳንክዋ አኩፎ አዶ አንዱ ሲሆኑ አፍሪካ እጅግ እያዘነች መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ አያይዘውም “መልሰው ደግሞ፣ የምጣኔ ሀብታችሁን በፍጥነት ለማሳደግ የገጠማችሁን እድል አትጠቀሙበትም ብለው የሚወቅሱን እነዚያው የበለጸጉ አገሮች ናቸው” ብለዋል፡፡

ትናንት በተጠናቀቀው ጉባኤ ላይ በዩናትይትድ ስቴትስና እንግሊዝ አስተባባሪነት፣ እኤአ እስከ 2030 ድረስ፣ የዓለም ሜቴን ልቀትን በ30 ከመቶ ለመቀነስ፣ የጉባኤው ተሳታፊ የነበሩት ከ100 በላይ አገሮች ስምምነቱን ፈርመዋል፡፡

በተደረጉ ስምምነቶች ላይ ሩሲያ፣ ቻያና፣ እና ብራዚል ያልፈረሙ ሲሆን፣ እነሱ ባልተሳተፉበት ሁኔታ፣ የዓለም ከባቢ አየር ሙቀትን እንዴት አድርጎ መቀነስ እንደሚቻል ጥያቄ አስነስቷል፡፡

XS
SM
MD
LG