በኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ላይ የሚፈፀም የዘፈቀደ እስር እና በአግባቡ የፍርድ ሂደት አለማግነት ከአራት አመት በፊት በሀገሪቱ መሻሻል አሳይቶ የነበረውን የፕሬስ ነፃነት ዳግም እንዲያሽቆለቁል እንዳደረገው በዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ተቋም ሲፒጄ የአፍሪካ ፕሮግራም አስተባባሪ አንጄላ ኩዊንታል ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። ትክክለኛ መረጃን ለህዝብ የሚያደርሱ ሚዲያዎች አለመኖር ህዝቡን ለሀሰተኛ መረጃዎች ያጋልጠዋል ሲሉም አስጠንቅቀዋል።
ስመኝሽ የቆየ በነዚህ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ከአንጄላ ኩዊንታል ጋር ቆይታ አድርጋለች።