በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በበጀት አፋፉ (ፊስካል ክሊፍ) ላይ ለመወሰን ኮንግረሱ ዛሬ ይሰበሰባል


የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሕግ መወሰኛው በሚቀርብለት የሕግ ረቂቅ ላይ ድምፅ ለመስጠት ዛሬ ከቀኑ ስምንት ሰዓት፣ በአዲስ አበባ አቆጣጠር ከምሽቱ አራት ሰዓት ላይ ይሰበሰባል፡፡




please wait

No media source currently available

0:00 0:08:58 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


የዩናይትድ ስቴትስ የፖለቲካ ሰዎች “ፊስካል ክሊፍ” ብለው የጠሩትን የሃገሪቱን በጀት አፋፍ የምክር ቤቱ እንደራሴዎች አንዳች ውሣኔ ላይ ሳይደርሱ በመቅረታቸው ባለፈው እኩለ ሌሊት ቀነ ገደቡን አሣልፋለች፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሕግ መወሰኛው በሚቀርብለት የሕግ ረቂቅ ላይ ድምፅ ለመስጠት ዛሬ በአዲስ አበባ አቆጣጠር ከምሽቱ አራት ሰዓት ላይ ይሰበሰባል፡፡

የሕግ መወሰኛው ትናንት ሲመክርበት ያመሸውን ሕግ ረቂቅ ዛሬ ማለዳ ላይ ባካሄደው ስብሰባው አፅድቆታል፡፡

ቀደም ሲል “ሁሉም፤ የፈለገውን ሁሉ አያገኝም” ያሉት ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ አቋማቸውን አለሣልሰው፤ አስቀምጠውት የነበረውን የገቢ ጣሪያ ለቤተሰብ ወደ 450 ሺህ ዶላር፤ የግል ገቢ ከሆነ ደግሞ ወደ 400 ሺህ ዶላር ከፍ እንዲል መስማማታቸውን አሣውቀዋል፡፡

የሕግ መወሰኛው የሁለቱም ወገን መማክርት ለዛሬው የተወካዮች ምክር ቤቱ ስብሰባ የሚያቀርቡትን ሃሣብ ያፀደቁት 89 ለ8 በሆነ ድምፅ እንደሆነ ታውቋል፡፡

ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማም ወዲያው ባሰሙት ድምፃቸው የሴኔቱን አባላት አሞግሰው የተወካዮች ምክር ቤቱ አባላትም የሴናተሮቹን አርአያ ተከትለው ሠነዱን እንዲያፀድቁ ጠይቀዋል፡፡

ዝርዝሩን ከዘገባው ያዳምጡ
XS
SM
MD
LG