በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢቦላ - በኮንጎ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፖብሊክ በምሥራቅ ግዛቷ ሲዛመት የቆየውና ባጠፋው ህይወት ብዛት ሁለተኛ የሆነው የኢቦላ ወረርሽኝ ማክተሙን ይፋ አደረገች።

ከ2 ዓመታት በፊት ምሥራቅ ኮንጎ ላይ የተቀስቀሰው ኢቦላ ቢያንስ 2ሺህ 280 ሰዎች ገድሏል።

ወረርሽኙ እንደተገታ የተናገሩት የሃገሪቱ የጤና ሚኒስትር ሲሆኑ የዓለም የጤና ድርጅትም ጄኔቫ ላይ አረጋግጦታል።

የድርጅቱ የአፍሪካ ዳይሬክተር ዶ/ር ማትሺዲሶ ሞኤቲ ወርርሽኙ በብዙ ትግል በቀጥጥር ሥር መዋሉን ጠቅሰው በትብብር በሳይንስ እና በቁርጠኝነት ማናቸውም ከባድ ወረርሽኝ መቆጠጠር እንደሚቻል ተስፋ የሚሰጥ ነው ብለዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የጤናና ሰብዓዊ አገልግሎት ሚኒስትር አሌክስ አዛር የኮንጎ ኢቦላ ወረርሽኝ ዩናይትድ ስቴትስ ቅድሚያ ትኩረት ከሰጠቻቸው የዓለምቀፍ ጤና ጉዳዮች እንዱ ሆኖ መቆየቱን አስታውሰው ለኮንጎና በጥረቱ የተሳተፉትን ወገኖች ሁሉ እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል።

XS
SM
MD
LG