በዐባይ ወንዝ የብዙ መቶ ዘመናት ታሪክ፣ የኢትዮጵያን የኃይል ጥማት ለማርካት እና ብሎም የክልሉን የኃይል አቅርቦት ያሳድጋል የተባለለት ግዙፉ የኅዳሴ ግድብሙሌት በመጨረሻው መጠናቀቁ መዘገቡን ተንተርሶ የተሰናዳ ውይይት ነው።
ይህንንም ተከትሎ፤ የዐባይን ወንዝ ያህል ዕድሜ የጠገበ "የዐባይን ልጅ ውሃ ጠማው" የሚል ተረት በእርግጥም ተረት ሆኖ ሊቀር ይሆን?” የሚል ጥያቄ ጋብዟል። ጥሙ ታዲያ የውሃ ብቻ አይደለም። ይልቁንም የኤክትሪክ መብራት ዛሬም ድረስ በየተራ እንደ ኩራዝ ብልጭ ድርግም የሚልበት፣ ለእድገት ወሳኝ የሆነው የኤክትሪክ ኃይል ከፍተኛ እጥረት ላለበት ሀገር የውሃውን ያህል ወሳኝ መሆኑ እሙን ነው።
የግዙፉ ግድብ ግንባታ ሥጋት ያሳደረባት እና ብርቱ ተቃውሞ ስታሰማ የኖረችው ግብጽ፣ የንዑስ አሕጉሩ የፖለቲካ ሁኔታ እና የኢትዮጵያ አጠቃላይ ይዞታ፣ ቀጣዩን ምዕራፍ እንደምን ይቀርጹት ይሆን?
የተሻሉ የሚባሉት ቀጣይ አቅጣጫዎችስ ምንድን ናቸው? ከሦስት የጉዳዩ አዋቂ ባለሞያዎች ጋር ተወያይተናል።
ክፍል አንድ - የዐባይ ጉዳይ - ተስፋ፣ ውዝግቦች እና ቀጣይ መንገዶች
ክፍል ሁለት - የዐባይ መውረጃ
መድረክ / ፎረም