በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሳምንቱ የራዲዮ መፅሔት ወጎች


የሳምንቱ የራዲዮ መፅሔት ወጎች
የሳምንቱ የራዲዮ መፅሔት ወጎች

የአድማጮች ማስታወሻ ነው። በሁለት የዓለም ጫፎች ያሉ (በሃሳብም ወደ ቀያቸው የሚጣሩ) የሁለት ዘመናት ለየቅል ገጠመኞች ትርክት ነው። እንደ አድራሽ መልዕክተኛም ከሁለቱ ቀዬዎች የሚያውሉን። አንድም ከምንኖርበት ሁለትም ከምናስበው።

በቀዳሚው የራዲዮ መጽሔት ገጽ (ከድምጹ ማጫወቻ) የሚያነቡት የቅርብ ሩቅድምጽ አሳዛኝም ተስፋ ለማድረግም በቂ ምክኒያት ያዘለ ከሚመስል ሰሞንኛ ጉዳይ ዙሪያ የሚያጠነጥን አንዲት የመካከለኛው ምዕራብ ዩናይትድ ስቴትሷ የሚነሶታ ክፍለ ግዛት ቤተኛ አድማጫችን ያደረሰችን ከማስታወሻዋ የሰፈረ ስዕል ነው።

የቅዳሜው ድንገት .. በአድማጭ ማስታወሻ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:01 0:00

የቀድሞው የኢትዮጵያ ዓየር ኃይል የጦር ተዋጊ ጄት አብራሪ (ዛሬ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የደሕንነት አገልግሎት የመስክ አስተባባሪ መኮንን ናቸው።) ዳዊት ወንድይፍራው ይባላሉ። ከተወለዱና ካደጉባት የአራት ኪሎዋ ግንፍሌ .. የዓየር በረራ ሃሁ እስከ ቀሰሙባት ክራስኖዳር ሶቭየት ሕብረት የዓየር ኃይል ኮሌጅ፤ የደብረዘይቱ የኢትዮጵያ ዓየር ኃይል ካምፕ .. ድሬዳዋ… ጎዴ .. አስመራ እና ሌሎች የተለያዩ የጦር አውድማዎች ..ከከሸፈው የመንግስት ግልበጣ ጉዳይ .. የስደት ሕይወት እና ለስደተኞች ደራሽ የመሆን ሥራ .. በሊቢያ .. ሶሪያ .. ቱርክ እና ሌሎች የዓለም አካባቢዎች .. “ያልታለመው የሕይወት መንገድ” በተሰኘው መጽሃፋቸው ያጏጉዙናል።

“ያልታለመው የሕይወት መንገድ” .. ቆይታ ከዳዊት ወንድአፈራው
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:41 0:00

ይኽኛው ደግሞ ብዙ ዘመናት ወደ አንድ ወደ ራቀና ለብዙዎች አድማጮቻችንም እንግዳ የሆነ የታሪክ የሚወስድ ነው። ሃሳቡ ግን ቅርብም የራስም ሊያደርጉት የሚጋብዝ ነው .. የባላንጣዎች ቡድን።

ይልማ አዳሙ ከምዕራብ ዩናይትድ ስቴትሷ የሎሳንጀለስ ከተማ ያደረሱን መጣጥፍ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ 2005ዓም የታተመ እና ለPultizer ሽልማት የበቃ መጽሃፍ ነው። .. “Team of Rivals: The Political Genius of Abraham Lincoln” ይሰኛል።

“የባላንጣዎች ቡድን”
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:06 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG