በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሊቢያ ተቀናቃኝ ቡድኖች ትሪፖሊ ውስጥ ከባድ ውጊያ አካሄዱ


ፎቶ ፋይል፦ በፓርላማ የተሾሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ፋቲ ባሻጋ እአአ የካቲት 10/2022
ፎቶ ፋይል፦ በፓርላማ የተሾሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ፋቲ ባሻጋ እአአ የካቲት 10/2022

ዛሬ ማክሰኞ ዋና ከተማዋ ላይ ውጊያ የተቀሰቀሰው በፓርላማው የተሾሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ፋቲ ባሻጋ ለመልቀቅ ፈቃደኛ አልሆን ካለው ተቀናቃኝ ቡድን ላይ የአስተዳደሩን ሥልጣን ለመውሰድ ሙከራ ማድረጋቸውን ተከትሎ መሆኑ ተዘግቧል።

ሁለቱ ተቀናቃኝ ቡድኖች ለሁለት ወር ያህል ከተፋጠጡ በኋላ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ትናንት ሌሊቱን ትሪፖሊ የገቡ ሲሆን መዲናዋን ከባድ ተኩስ ሲያናውጣት ከጥቂት ሰዓት በኋላ መውጣታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት አመልክቷል።

ቀውሱ ለሁለት ዓመታት ያህል አንጻራዊ ሰላም ያገኘችውን ሀገር ወደተራዘመ ውጊያ ሊመልሳት ይችላል የሚል ሥጋት ፈጥሯል።

XS
SM
MD
LG