በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና ለአፍሪካ ሀገራት የዕዳ ስራዛና የገንዘብ ድጋፍ ልታደርግ ነው

ቻይና ከኢንዱስትሪ ማዳበር እስከ መሰረተ ልማት ዝርጋታ ድረስ በሚካሄድ የዕድገት ሥራ ላይ የሚልውል አዲስ 60 ቢልዮን ዶላር ለአፍሪካ እንደመታቀርብ አስታውቃለች። በያዝነው ዓመት ማብቅያ ገደማ ከወለድ ነፃ የሆኑ ብድሮች በምትሰጥበት ወቅት የአንዳንድ የአፍሪካ ሀገሮች ብድሮች እንደሚሰረዙም ገልፃለች።

ቻይና ከኢንዱስትሪ ማዳበር እስከ መሰረተ ልማት ዝርጋታ ድረስ በሚካሄድ የዕድገት ሥራ ላይ የሚልውል አዲስ 60 ቢልዮን ዶላር ለአፍሪካ እንደመታቀርብ አስታውቃለች። በያዝነው ዓመት ማብቅያ ገደማ ከወለድ ነፃ የሆኑ ብድሮች በምትሰጥበት ወቅት የአንዳንድ የአፍሪካ ሀገሮች ብድሮች እንደሚሰረዙም ገልፃለች።

የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ዢንፒንግ ዛሬ ይህን ቃል የገቡት በዢንግ ላይ የተጀመረው የቻይናና የአፍሪካ የትብብር መድረክ ጉባዔ ሲከፈት ባደረጉት ንግግር ነው።

ዕዳ የሚሰረዝላቸው የአፍሪካ ሃገሮች የትኞቹ እንዳሆኑ አልተናገሩም። ይሁንና ዕርምጃው በአህጉሪቱ ያለው የዕዳ ብዛት ሥጋትንና “በዕዳ የመተብተብ ዲፕሎማሲ” አደጋን አቅጣጫ ለማስቀየር ይመስላላ ተብሏል።

ከ30 በላይ የሚሆኑ የአፍሪካ ሀገሮች መሪዎች በተሰበሰቡበት ታላቁ ሕዝባዊ አዳራሽ ላይ ሺ ባደረጉት ንጝር ቻይና በአፍሪካ የምታደርገው የመዋዕለ ነዋይ ፍስተና ከአህጉሪቱ ጋር የሚኖራት ግንኙነት ይቀጥላል ብለዋል። ሀገራቸው በአፍሪካ የምታፈሰው መዋዕለ ነዋይ ከፖለቲካዊ ክሮች ጋር እንደማይያዝይዝም አስገንዝበዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG